Ethiopian Election 2021

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ (ምርጫ 2013)

7.4 ሚሊዮን ብር ለግል ተወዳዳሪዎች ሊሰጥ ነው

ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 16, 2021)፦ በዘንድሮው ምርጫ 2013 በግል ተወዳዳሪ የኾኑ እጩዎች ለእያንዳንዳቸው 50 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግላቸው መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። በዘንድሮው ምርጫ በግል ለመወዳደር የተመዘገቡት እጩዎች 148 ናቸው።

ቦርዱ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ለግል እጩ ተወዳዳሪዎች ባስተላለፈው መልእክት የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አምኖበት፤ ለእያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ድጋፍ ለመስጠት ቦርዱ ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታውቋል።

በዚህም መሠረት ለ148 የግል ተወዳዳሪዎች ሰባት ነጥብ አራት ሚሊዮን (7.4) ብር ቦርዱ ለእጩዎቹ ወጪ እንደሚያደርግ ታውቋል። የቦርዱ አጭር መልእክት ይህንን ይመስላል። (ኢዛ)

መረጃ ለግል እጩ ተወዳዳሪዎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከግል እጩ ተወዳዳሪዎች ጋር በተለያየ ግዜ ባደረገው ምክክር መሠረት፤ ቦርዱ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አምኖበት ለእያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ድጋፍ ለመስጠት ወስኗል።

ስለኾነም በምርጫ ቦርድ በግል እጩ ተወዳዳሪነት እውቅና አግኝታችሁ ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የምትወዳደሩ ሁሉ፤ ሙሉ ስማችሁን፣ አድራሻችሁን (ስልክ ቁጥራችሁን፣ ኢሜል) እንዲሁም የባንክ አካውንታችሁን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ሥራ ክፍል በአካል ወይም በ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ኢሜል አድራሻ ወይም በስልክ ቁጥሮች +251913551505/ +251929289444 የዋትስ አፕ እና ቴሌግራም አፕሊኬሽኖች ላይ እንድትልኩ እናሳውቃለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሰኔ 9 ቀን 2013 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ