Ethiopian Airlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ

አየር መንገዱ በማንም የጦር መሣሪያ የማጓጓዝ አገልግሎት ተጠይቆ እንደማያውቅ ገልጿል

ኢዛ (ዓርብ ሰኔ ፲፩ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 18, 2021)፦ በአፍሪካ ቀዳሚ የአየር ትራንስፖርት በመስጠት የሚታወቀው አንጋፋው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ የጦር መሣሪያ ያጓጉዛል በሚል ቀርቦብኛል ያለውን ትችት ሐሰት ነው አለ። አየር መንገዱ በግለሰብም ኾነ በተቋም ደረጃ የጦር መሣሪያ የማጓጓዝ አገልግሎት ተጠይቆም እንደማያውቅ ገልጿል።

አየር መንገዱ በመረጃ ገጹ እንዳመለከተው፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጦር መሣሪያ ያጓጉዛል ብለው መረጃ ያሰራጩትን አካላት ባይገልጽም፤ በአንዳንድ ወገኖች እንዲህ ባለ መልኩ መገለጹን ፍጹም ሐሰት መኾኑን አመልክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍም ኾነ በአገር ውስጥ በረራው አንዳችም የጦር መሣሪያ ያላጓጓዘ እና የማያጓጉዝ መኾኑን አጽንኦት ሰጥቶ የገለጸው የአየር መንገዱ፤ አንዳንድ ወገኖች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚያናፍሱትን ያልተገባ ተግባር ያቁሙም ብሏል።

አየር መንገዱ የማንኛውንም ግለሰብም ኾነ ተቋም የጦር መሣሪያ አጓጉዞ እንደማያውቅ እንዲሁም እንዲህ ዐይነት አገልግሎት እንዲሰጥ እንኳን ተጠይቆ እንደማያውቅም አመልክቷል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ