Danile Bekele (PHD), Ethiopian Human Rights Commission

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ (የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮምሽን ዋና ኮሚሽነር)

የሦስት የዘርፍ ኮሚሽኖችም ሹመት ጸደቀ

ኢዛ (ዓርብ ሰኔ ፲፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. June 25, 2021)፦ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንን (ኢሰመኮን) በምክትል ኮሚሽነርነት እና በተለያዩ ዘርፎች ኮሚሽን ኾነው የሚያገለግሉ ተሿሚዎች ሹመት ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ።

በዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሚመራውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን በተለያዩ የኃላፊነት ደረጃዎች እንዲመሩ ዛሬ ዓርብ ሰኔ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. ሹመታቸው ከጸደቀላቸው ውስጥ ወ/ሮ ራኬብ መለስ የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ኾነዋል።

ወ/ት እርግብ ገብረሐዋርያ ደግሞ የአካል ጉዳታኞች እና አረጋውን መብቶች ኮሚሽነር ኾነው እንዲያገለግሉ ተሹመዋል።

የኮሚሽኑ የፖለቲካ መብቶች ጉዳዮች ኮሚሽነር እንዲኾኑ የተሾሙት ዶ/ር አብዲ ጅብሪል ናቸው። የኮሚሽኑ የሴቶች እና ሕፃናት መብቶች ጉዳዮች ኮሚሽነር ኾነው እንዲያገለግሉ የተሾሙት ደግሞ ወ/ሮ መስከረም ገስጥ ናቸው። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ