Lidetu Ayalew (L), Ethiopian Human Rights Commission (M), Dr. Daniel Bekele (R)

አቶ ልደቱ አያሌው (በግራ)፣ ኢሰመኮ (መኻል)፣ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ (በቀኝ)

“አላስፈላጊ እስር ማስቀረትና የሰብአዊ መብት ይከበር!” ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

ኢዛ (ሐሙስ መስከረም ፲፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. September 24, 2020)፦ በፍርድ ቤት ውሳኔ በ100 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ የተወሰነላቸው አቶ ልደቱ አያሌው፤ ያለምንም ቅድመ ሁኔት ከእስር መፈታት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አሳሰቡ።

ኮሚሽነሩ ዶ/ር ዳንኤል የምሥራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱን በ100 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ ትእዛዝ የሰጠ ቢኾንም፤ እስካሁን አለመፈታታቸው ተገቢ ያለመኾኑን በመጠቆም፤ “የፍርድ ቤት ውሳኔ አለማክበር ለሰብአዊ መብቶች መከበር አደጋ ነው” ብለዋል።

በዚሁ ጉዳይ ላይ በሰጡት አስተያየት፤ “የሰብአዊ መብቶች መከበር ዋና ዋስትናው የፍርድ ቤት ውሳኔ መከበር በመኾኑ፤ አቶ ልደቱ አያሌውን ጨምሮ በፍርድ ቤት የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸውና የዋሰትና ሁኔታውን አሟልተው ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ትእዛዝ የሰጠላቸው ታሳሪዎች በሙሉ በአስቸኳይ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከእስር ሊፈቱ ይገባል” ብለዋል።

አቶ ልደቱ በ100 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲለቀቁ ትእዛዝ የተሰጠው መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደነበር አይዘነጋም። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ