ተጠባቂው የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ማብራሪያ በትግራይ ጉዳይ ላይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ
ከትግራይ ጉዳይ ጋር ተያይዞ መንግሥት እየወሰደ ያለው እርምጃ
ኢዛ (እሁድ ሰኔ ፳፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 4, 2021)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ ነገ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገለጸ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በነገው ዕለት (ሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም.) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሰጣሉ ተብሎ የሚጠበቀው ማብራሪያ በዋነኝነት ከትግራይ ክልል ጉዳይ ጋር እና ከዚሁ ጋር ተያይዞ መንግሥት እየወሰደ ያለው እርምጃ ላይ ይኾናል። (ኢዛ)