Office of the Mayor Addis Ababa

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት

ከ2013 በጀት ዓመት አንጻር ሲታይ የ15 በመቶ ብልጫ ያለው ነው

ኢዛ (ማክሰኞ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 13, 2021)፦ ተሰናባቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ለ2014 በጀት ዓመት 70.07 (ሰባ ነጥብ ዜሮ ሰባት) ቢሊዮን ብር በጀት በማጽደቅ የሥራ ጊዜውን አጠናቀቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ (ማክሰኞ ሐምሌ 6 ቀን 2013 ዓ.ም.) የቀጣዩን 2014 በጀት ዓመት አስመልክቶ ተወያይቶ የጸደቀው በጀት ከ2013 አንጻር ሲታይ የ15 በመቶ ወይም የ9.31 (ዘጠኝ ነጥብ ሦስት አንድ) ቢሊዮን ብር ብልጫ ያለው ነው።

በጸደቀው በጀት መሠረት በአዲስ አበባ ደረጃ ለሚገኙ የማዕከል መሥሪያ ቤቶች 46.55 (አርባ ስድስት ነጥብ አምስት አምስት) ቢሊዮን ብር የተመደበ ሲሆን፤ ይህም ከጠቅላላው በጀት 66.8 (ስድሳ ስድስት ነጥብ ስምንት) በመቶ የሚኾነውን ድርሻ የሚይዝ መኾኑን ነው። ለክፍለ ከተሞች ደግሞ 24.1 (ሃያ አራት ነጥብ አንድ) ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት የተያዘ ሲሆን፤ ይህም ከጠቅላላ በጀቱ 34.12 (ሰላሳ አራት ነጥብ አንድ ሁለት) በመቶ ድርሻ አለው።

በመረጃው መሠረት የ2014 በጀት ዓመት በጀት ከቀረጥ እና ቀረጥ ካልኾኑ ከመዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች እንዲሁም ከብድር እና እርዳታ የሚሸፍን ይኾናል።

ከ2013 በጀት ዓመት የተረፈ በጀትም ለ2014 በጀት ዓመት መሸፈኛ ይውላል ተብሏል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!