Prof. Beyene Petrosአማካሪ ሆነው ያገለግላሉ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 1 ቀን 2001 ዓ.ም. May 9, 2009)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ሕብረትን ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ በሊቀመንበርነት ሲመሩ የቆዩት ፕሮፌሠር በየነ ጴጥሮስ ሥልጣን ለቀቁ።

 

ፕሮፌሠር በየነ ሥልጣናቸውን የለቀቁት ባለፈው ሣምንት በኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በተካሄደው የድርጅቱ ሦስተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በተካሄደው ምርጫ ነው።

 

137 የድርጅቱ አባላት በጉባዔው ላይ ተሳትፈው ፕሮፌሠር በየነ እና አቶ ሙሉ መጃ የድርጅቱ አማካሪዎች ሆነው እንዲያገለግሉ የሰየሟቸው መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።

 

የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ሕብረት አዲስ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ጥላሁን እንደሻው እንደገለጡት ድርጅቱ ከ1995 ዓ.ም. እስከ ዛሬ በየሁለት ዓመቱ ማድረግ የነበረበትን ጠቅላላ ጉባዔ ሳያካሂድ የቆየው በሚያጋጥሙት ችግሮችና መወጣት ባለበት ተግባር ምክንያት ምቹ ጊዜ ባለማግኘቱ ነው።

 

“ከ1986 ዓ.ም. በኋላ ያለው ደቡብ ሕብረት በግለሰቦች የተመሰረተ ፓርቲ እንጂ ሌላ አይደለም” ያሉት አቶ ጥላሁን ፓርቲው ለምርጫ ቦርድ ባቀረበው የምዝገባ ጥያቄ በመስራችነት የሰጠው የስም ዝርዝር ከሕብረቱ መሥራች ድርጅቶች የተገኘ እንደሆነ አስታውቀዋል።

 

አቶ ጥላሁን ድርጅቶቹ አባላቱን ለፓርቲው ምሥረታ አሳልፈው ከሰጡ በኋላ፣ የአንዳንዶቹ ያለ መክሰም የድርጅቱ ጉዳይ አለመሆኑን አመልክተው፤ ፓርቲው ነፃና ሕጋዊ አካል መሆኑን አስገንዝበዋል።

 

የደቡብ ሕብረት ድርጅቶች የተሰበሰቡበት ግንባር ወይም ጥምረት ሳይሆን እንደማንኛውም ፓርቲ በግለሰቦች አባልነት የተቋቋመና የተደራጀ ፓርቲ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ጥላሁን፣ ደቡብ ሕብረት በተመሰረተበት ወቅት በመስራችነት የተሳተፉ አንዳንድ ድርጅቶች አመራሮች አሁንም ድርጅቶቻቸውን ይዘው እንደሚገኙ እና ሕብረቱ እነዚህን እንደ አጋር ፓርቲ እንደሚያያቸው ገልጠዋል።

 

የብሔረሰቡም ምሁራን ወደ ድርጅቱ እንዳልተሳቡ ገልጸው፤ ምሁራኑን ወደ ድርጅቱ መሳብ ተቀዳሚ የአመራሩ ሥራ መሆኑን፣ አዳዲስ ቢሮዎችን መክፈትና ህዝብን ማደራጀት ጊዜ የሚሰጥ ሥራ እንደሆነ አቶ ጥላሁን ዘርዝረዋል።

 

አቶ ጥላሁን ድርጅቱ ለ2001 እና ለ2002 ዓ.ም. የያዛቸውን ዕቅዶች እንደሚጠበቅም አያይዘው ገልፀዋል። አቶ ጥላሁን መድረክ ለዲሞክራሲ ምክክር በኢትዮጵያ ፀሐፊ ሆነው እየሠሩ መሆኑም ታውቋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ