ፖሊስ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠየቀባቸው

Ethiopia Zare (ሰኞ ግንቦት 3 ቀን 2001 ዓ.ም. May 11, 2009)፦ ከግንቦት ሰባት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ከታሰሩት 40 እስረኞች ውስጥ 36 የሚሆኑት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ ግንቦት 3 ቀን 2001 ዓ.ም. ቀርበው ጉዳያቸው በዝግ መታየቱን የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።

 

በዛሬው ዕለት (ሰኞ ግንቦት 4 ቀን 2001 ዓ.ም.) እስረኞቹ በአንድ ላይ ሳይሆን ሁለት ሁለት እየሆኑ በካቴና ታስረው ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው በዝግ ችሎት የታየ ሲሆን፣ ምንጮች እንደጠቀሱት ፖሊስ የ14 ቀን ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል።

 

ተጠርጣሪዎቹን አስመልክቶ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትና የፌደራል ፖሊስ የጋራ ፀረ-ሽብር ግብረ ኃይል “የመንግሥት ግልበጣ ሊያካሂዱ ሲሉ ያዝኳቸው” ሲል ሚያዝያ 17 መግለጫ ካወጣ በኋላ፤ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን ደግሞ አርብ ሚያዝያ 23 ቀን “የግድያና የሽብር ተግባር ሊፈጽሙ ሲሉ ያዝናቸው” ማለታቸውን መዘገባችን አይዘነጋም።

 

ግንቦት ሰባት የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በበኩሉ ሚያዝያ 17 ቀን መግለጫ ማውጣቱንና መግለጫውን ማስነበባችን ይታወሳል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ