ከፍተኛ ንብረት ወድሟል

Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 23 ቀን 2001 ዓ.ም. May 31, 2009)፦ ዛሬ ጠዋት ከቀኑ አራት ሰዓት አካባቢ በተነሳ ቃጠሎ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጎን የሚገኘው ዋናው የቴሌ ኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ህንጻ በተነሳ ቃጠሎ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን ምንጮቻችን ገለጹ።

 

በህንጻው አራተኛ ፎቅ አካባቢ ቃጠሎው መነሳቱን የገለጹት ምንጮች የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ ከመሆኑ ሌላ በምን ያህል ገንዘብ የሚገመት ንብረት መውደሙን ለመግለጽ የማይቻል መሆኑን ተናግረዋል።

 

ቃጠሎው የተነሳበት ምክንያት እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን፣ በህንጻው የሥራ ቀን ባለመሆኑ ምክንያት ሠራተኞ ባለመኖራቸው በሰው ላይ ጉዳት አለመድረሱን ለማወቅ ተችሏል። በቃጠሎው ምክንያት በስልክ ላይ ሊደርስ የሚችል ችግር እንደሌለ የተገለጸ ሲሆን፣ ጠቅላላ በመስሪያ ቤቱ ሂደት ላይም ሆነ የስልክ መስመር ላይ ሊደርስ የሚችለውን ችግር በሚመለከት በቀጣይ ቀናቶች እንደሚገለጽ ታውቋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ