ሦስቱ ታስረው፣ ቃላቸውንና አሻራ ሰጥተው በዋስ ተለቀቁ

Ethiopia Zare (ቅዳሜ የካቲት 29 ቀን 2000 ዓ.ም. March 8,2008) "ፎርቹን" የተሰኘው በኢኮኖሚ ላይ የሚያተኩረውና በየሣምንቱ ዕሁድ እየታተመ የሚወጣው ጋዜጣ አምስት አዘጋጆች ተከሰሱ። ጋዜጣው ስሜን አጥፍቶ ኪሳራ አድርሶብኛል ሲል በድጋሚ የከሰሳቸው አያት አክሲዮን ማኅበር መሆኑን ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ አስረዳ።

 

አያት አክሲዮን ማኅበር በድጋሚ ክሱን የመሰረተው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፍትሐ ብሔር ችሎት "ፎርቹን ጋዜጣ ስሜን አጥፍቶ ኪሳራ አድርሶብኛል" በሚል  መሆኑ ታውቋል።

 

የጋዜጣውን ባለቤትና ማኔጂንግ ኤዲተር ጨምሮ ሦስቱ ጋዜጠኞች ረቡዕ ዕለት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የኢኮኖሚ ወንጀል ምርመራ መምሪያ በቁጥጥር ስር ውለው፣ ቃላቸውን ከሰጡና አሻራ ከተነሱ በኋላ በዋስ ተለቀዋል።

 

ክሱ የቀረበባቸው አምስት ጋዜጠኞች ቢሆኑም ከአ.አ. ፖሊስ ኮሚሽን የኢኮኖሚ ወንጀል ምርመራ መምሪያ መጥሪያ ደርሷቸው የቀረቡት የጋዜጣው ባለቤትና ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው ጋዜጠኛ ታምራት ገ/ጊዮርጊስ፣ የጋዜጣው ም/ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኢሣያስ መኩሪያ እና የጋዜጣው ሪፖርተር ጋዜጠኛ ውድነህ ዘነበ መሆናቸውን ለማወቅ ችለናል። ሁለቱ ተከሳሾች ግን ከጋዜጣው ዝግጅት ክፍል የለቀቁ በመሆኑ ሳይቀርቡ ቀርተዋል።

 

አያት አክሲዮን ማኅበር "ፎርቹን" የተባለው ጋዜጣ በጋዜጣው ላይ በከፈተው ዘመቻ ስሜን አጥፍቶ ለኪሳራ ዳርጎኛል ሲል በ20.4 ሚሊዮን ብር በፍትሐ ብሔር ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

 

ፎርቹን ጋዜጣ ከተመሠረተ ከስንምት ዓመት በላይ የሆነው ጋዜጣ እንደሆነ ይታወቃል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ