ዘጠኝ እስረኞች በሦስት መዝገብ

ጽዮን ግርማ (አዲስ አበባ)

Ethiopia Zare (ሰኞ ሚያዝያ 21 ቀን 2006 ዓ.ም. April 28, 2014)፦ ባለፈው ሳምንት ወደ ማእከላዊ እስር ቤት የተጣሉት ስድስት  የ'ዞን ዘጠኝ' አባላትና ሶስት ጋዜጠኞች ሁኔታ አነጋጋሪ ሆኖ መሰንበቱ ይታወቃል። በአሁኑ ሰአት እስረኞቹ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ሲሆን ክስም እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል። ሁኔታውን ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ በፌስ ቡክ ገጿ እንደሚከተለው ዘግባዋለች።

የማዕከላዊ ወንጅል ምርመራ ፖሊስ በትናንትናው (እሁድ) ዕለት ጠዋት አራዳ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት አቅርቦ የጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡ በሦስት መዝገብ የጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀባቸው ዘጠኝ ጸሐፊዎች አገሪቷን በሶሻል ሚዲያ ለማተራመስ ራሱን የመብት ተሟጋች ነኝ ብሎ ከሚጠራ የውጭ ኃይል ጋር በሐሳብም በገንዘብም ተረዳድተውና ተስማተው በአገሪቷ ላይ የብጥብጥ ቅስቀሳ ለማነሳሳት አቅደው ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸው በቁጥጥር ውለዋል ይህንንም በሚመለከት መረጃ እስክናሰባስብ ጊዜ ይሰጠን በሚል የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸዋል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ መንግስት በረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ላይ ክስ መሰረተ

በተመስገንደሳለኝ (አዲስ አበባ)

- ከ253, 336 ከ42 ሳንቲም ዩሮ በላይ ኪሳራ ደርሷል ተብሏል

- የአእምሮ ችግር እንዳሌለበትም ተረጋግጧል

ፍትሕ ሚኒስቴር በረዳት አብራሪ ኃይለመድን አበራ ላይ የካቲት 9 ቀን 2006 ዓ.ም ሌሊት የበረራ ቁጥር ET 702 የሆንን ቦይንግ አውሮፕላንን ከእነ 202 ተሳፋሪዎቹ ወደ ሮም በሚበርበት ወቅት ጠልፎ ሲውዘርላንድ አሳርፏል በማለት በከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ክስ መመስረቱን የፍትሕ ሚኒስቴር ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መንግስት በጎንደር ለምርጫ ቅስቀሳ 8ሺህ ብር እያደለ ነው

አምስት የአንድነት ፓርቲ አባላት ታስረዋል

Ethiopia Zare (ቅዳሜ መጋቢት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. March 29, 2014)፦ ዛሬ ገዥው ፓርቲ በጎንደር ከተማ አደባባይ እየሱስ በጠራው ስብሰባ ለእያንዳንዳቸው ተሰብሳቢዎች 8ሺህ ብር ብድር በመስጠት መጭውን ምርጫ ግን ኢህአዲግን እንዲመርጡ በመቀስቀስ ላይ ባለበት ወቅት ምርጫን በገንዘብ መግዛት አይቻልም ብለው ጥያቄ ያቀረቡ አምስት የአንድነት ፓርቲ አባላት መታሰራቸውን አቶ ሃብታሙ አያሌው ዛሬ ይፋ አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአንድነት ፓርቲ መሪ ኢ/ር ግዛቸው በውጭ ሀገር ያሉ ደጋፊዎች ጋር በስልክ ውይይት አደረጉ

በዉጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በአካል ርቆ ቢገኝም ልቡ አገር ቤት ነዉ።ኢ/ር ግዛቸው 

 አንድነት ፓርቲ በ450 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ለመወዳደር እቅድ አለው

Ethiopia Zare ሰኞ ካቲት 24 ቀን 2006 ዓ.ም. March 3, 2014)፦ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር፣ በአሜሪካ ካሉ የድጋፍ ማህበራት ጋር ወደ ሁለት ሰዓት የሚጠጋ ሰፊ ዉይይት በቴሌኮንፈራንስ አደረጉ። ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራዉ ፣ የአንድነት ፓርቲ እያደረጋቸው ስላለው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች ሰፋ ያለ ሃታተ የሰጡ ሲሆን፣ ከስብሰባው ተሳታፊዎች በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወጣቱ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ቦሌ መንገድ ላይ ራሱን አጠፋ

ጽዮን ግርማ
በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው
Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. Feb. 24, 2014)፦ ዛሬ በምሳ ሰዓት አካባቢ፤ በሱፍቃድ በጋሻው የተባለ ዕድሜው በሃያዎቹ ውስጥ የሚገመት ወጣት በቦሌ መንገድ ላይ ከአራት ጊዜ በላይ በተከታታይ ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን አጠፋ። ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ”ኑሮ መሮኛል” ሲል ተሰምቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሲድኒ ኢትዮጵያዊያን የተሳካ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

አዲሱ አምባሳደር ሀፍረት ገጠማቸው

አቢይ አፈወርቅ
በሲድኒ የኢትዮጵያዊያን የተቃውሞ ሰልፍ
Ethiopia Zare (ቅዳሜ የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም. Feb. 22, 2014)፦ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አረጋ ሀይሉ ትላንት (ቅዳሜ ፌብሯሪ 22 ቀን) የሲድኒ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያንን በልማት ዙሪያ ለማነጋገር የያዙት ፕሮግራም በአሳፋሪ ሁኔታ ተደመደመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ህወሃት/ኢህአዴግ በሲድኒ የጠራው ስብሰባ በተቃውሞ ተወጥሯል

አርቲስት አይናለም ተስፋዬን ጨምሮ 12 ሰዎች ብቻ ወደ አዳራሹ ገብተዋል
Ethiopia Zare (አርብ የካቲት 14 ቀን 2006 ዓ.ም Feb. 17, 2014)፦ በአውስትራሊያዋ ሲድኒ በአምባሳደር አረጋ ሃይሉ የተጠራው ልማታዊ ውይይት በሲድኒ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ በማሰማት ላይ መሆንቸውንና የመንግስት ደጋፊዎች በቦታው ለመታየት እንዳልቻሉ ለማወቅ ተቻለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ31 ዓመቱ ወጣት ረዳት አብራሪ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላንን ጠለፈ

ጠላፊው ለአምስት ዓመታት በአየር መንገዱ አገልግሏል”መንግሥት

”በጠለፋው ሳይሆን ተሳፋሪዎቹን በማገቱ እስከ 20 ዓመት ሊያሳስር የሚችል ክስ ሊመሰረትበት ይችላል”የስዊስ አቃቤ ሕግPolice search passengers after helping them disembark from the hijacked Ethiopian Airlines flight

Ethiopia Zare (ሰኞ የካቲት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. Feb. 17, 2014)፦ ዛሬ ጠዋት ሮም ሊገባ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ”ኢቲ 702” በ31 ዓመቱ ረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ተገኝ ተጠልፎ በስዊዘርላንድ፤ ጄኔቭ ከተማ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ አረፈ። በጣሊያንና ስዊዘርላንድ ድንበር አካባቢ ሲደርስ በሁለት ተዋጊ ጀቶች ታጅቦ የነበረ ሲሆን፣ ረዳት አብራሪው በስዊዘርላንድ ጥገኝነት ጠይቋል። ተሳፋሪዎቹ አውሮፕላኑ መጠለፉን አያውቁም ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፍቃዳቸው ከሥልጣናቸው ለቀቁ

Alemayehu Atomssa, አቶ አለማየሁ አቶምሳEthiopia Zare (ሰኞ የካቲት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. Feb. 17, 2014)፦ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አለማየሁ አቶምሳ በገዛ ፈቃዳቸው ከኦሕዴድ ሊቀመንበርነታቸው ለቀቁ። በዛሬው ዕለት በተካሄደው የኦሮሞ ሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ መልቀቂያቸውን ያስገቡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ጥያቄያቸው ተቀባይነት አግኝቶ ከሥልጣን መነሳታቸው ታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሸንጎ 'በአማራው' ላይ ያነጣጠረውን የዘር ጥላቻ አወገዘ

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) Ethiopian People's Congress for United Struggle (Shengo)Ethiopia Zare (ረቡዕ የካቲት 5 ቀን 2006 ዓ.ም. Feb. 12, 2014)፦ የአማራ ክልል ም/ፕሬዝዳንት አቶ አለምነው መኮንን በአማራው ላይ የሰነዘሩትን ፀያፍና በዘር ጥላቻ ላይ ያዘነበለ ስድብ በማውገዝ፤ "የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ" ትናንት የካቲት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. መግለጫ አወጣ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ