በቫንኩቨር በሳኡዲ አረቢያ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኞች 10 ሺህ ዶላር ተሰበሰበ

Ethiopia Zare (እሁድ ጥቅምት 11  ቀን 2006 ዓ.ም. Jan 18, 2014)፦ በሳኡዲ አረቢያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያኖች ያሉበት አሳሳቢ ሁኔታ ያስጨነቃቸው በቫንኩቨር ካናዳ ነዋሪዎች ምሽቱን ባደረጉት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ወደ 10ሺህ ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ማሰባሰባቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አርኤል ሻሮን ዛሬ አረፉ

እስራኤልን ለአምስት ዓመታት መርተዋል
አርኤል ሻሮን  Ariel SharonEthiopia Zare (ቅዳሜ ጥር 3 ቀን 2006 ዓ.ም. Jan 11, 2014)፦ የእስራኤል የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩትና ሀገሪቷን ለአምስት ዓመታት ያህል የመሩት አርኤል ሻሮን በሰማንያ አምስት ዓመታቸው ዛሬ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፈረሰኛ ሻምበል ማሩ መልካ በ87 ዓመታቸው አረፉ!

ፈረሰኛ ሻምበል ማሩ መልካ Maru Melkaየቀብር ስነ ስርአታቸው ዛሬ በየካ ሚካኤል ይፈጸማል

Ethiopia Zare (ረቡዕ ታህሣስ 30 ቀን 2006 ዓ.ም. Jan 8, 2014)፦ በፈረስ ግልቢያ ስፖርት ታሪክ ውስጥ በአስተማሪነት፣ በስፖርተኝነትና በርካታ ሽልማቶችን በመቀዳጀት ግምባር ቀደም ተጠቃሽ የሆኑት ፈረሰኛ ሻምበል ማሩ መልካ በ87 ዓመታቸው ታህሣስ 29 ቀን 2006 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ ሲሆን ዛሬ የቀብር ስነ ስርአታቸው በአዲስ አበባ የካ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንደሚፈጸም ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

17ኛው ዓመት የኢትዮጵያዊያን ስፖርት ውድድር በድምቀት ተከናወነ!

በአውስትራሉያ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን መካከል በየዓመቱ የሚደረገው የስፖርት ውድድር ዘንድሮም ለ17ኛ ግዜ ከዲሴምበር 24 እስከ 29 ባለት 6 ቀናት በድምቀት ተከናውኗል። በዘንድሮው ውድድር ከመቼውም ግዜ በበለጠ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኢትዮጵያዊ የተሳተፈበት ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታላቁ የነፃነት አባት ኔልሰን ማንዴላ አረፉ (1918-2013)

የዓለማችን ታላቁ የፀረ-አፓርታይድ መሪ
ኒልሰን ማንዴላ Nelson Mandela

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሕዳር 26 ቀን 2006 ዓ.ም. Dec 5, 2013)፦ አፓርታይድን ከምድረ ደቡብ አፍሪካ እስከመጨረሻው ለመገርሰስ በተደረገው ታላቅ ተጋድሎ በዋንኛነት ተጠቃሽ የነበሩትና የሰላም አባት በመባል ዓለም አቀፋዊ ሽልማቶችን የተጎናጸፉት የደቡባዊት አፍሪካ የነፃነት አባት ኔልሰን ማንዴላ አረፉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በካናዳዋ የንግድ መናገሻ ቶሮንቶ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠራ

የሕግ ባለሙያው ዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ ንግግር ያደርጋል

አሁንም የኢትዮጵያዊያኖች የድረሱልኝ ጥሪ እየተሰማ ነው

Ethiopia Zare (ሐሙስ ኅዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም. November 14, 2013)፦ በካናዳ የንግድ መናገሻ በሆነችው ቶሮንቶ ከተማ በሳኡዲት አረቢያ በኢትዮጵያዊያኖች ላይ የሚፈጸመውን ግፍ በመቃወምና በአሰቃቂ ሁናቴ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የሻማ ማብራት ስነስርአት ነገ አርብ እንደሚካሄድ ይፋ ተደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያን መንግሥት ፍርድ ቤት ለማቅረብ እንቅስቃሴ ተጀመረ

ጠበቃ ስቴላ ያርዴእንቅስቃሴውን የጀመሩት ስዊድናዊ ጠበቃ ከኢትዮጵያውና ጋር ውይይት አደረጉ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ኅዳር 3 ቀን 2006 ዓ.ም. Nov. 12, 2013)፦ ባለፈው ቅዳሜ ጥቅምት 23 ቀን 2006 ዓ.ም. (ኖቬምበር 2 ቀን 2013) የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የወያኔን መንግሥት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተጀመረውን ክስ መነሻ በማድረግ የክሱን ሂደት ከሚመሩት ከስዊድናዊው ጠበቃ ከስቴላ ያርዴ እና ከሌሎች እንግዶች ጋር በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ወይይት አደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል መልእክት ለባለቤቷና ለህሊና እስረኞች

Ethiopia Zare (አርብ ጥቅምት 23 ቀን 2006 ዓ.ም November 1, 2013):- ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል በእስር ላይ የሚገኘውን የብእር ሰው፣ ጋዜጠኛና የፖለቲካ ተንታኝ ባለቤቷን እስክንድር ነጋን ተለይታ ከምትኖርበት ዋሽንግተን ዲሲ የሀገሯን የመጨረሻ ስንብት በሚመለከት ለህሊና እስረኞች ለሆኑት ታሳሪዎች ያስተላለፈችው መልእክት ይፋ ተደረገ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሲያትል የሃና ገዳዮች 37 እና 29 አመት ፍርድ ተወሰነባቸው

"ኢትዮጵያዊያን በፍርዱ ረክተዋል" ወ/ሮ ሙሉመቤት ረታ (በሲያትል የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር)

"በእኔ አስተያየት ፍትህ ተበይኗል፤ ዳኛዋም ሆኑ ፍርድ ሰጭዎቹ (ጁሪዎቹ) በትክክል ጉዳዩን አይተው ወስነዋል ብየ አምናለሁ" ዶ/ር ሸክስፒር ፈይሳ

Ethiopia Zare (ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. October 30, 2013)፦ ከሁለት ዓመት በፊት ሃና ዊሊያምስ የተባለችውን ታዳጊ በቅዝቃዜ ደጅ ላይ በማዋልና በማሳደር አሰቃይተው ገድለዋል የተባሉት አሳዳጊዎቿ ኬሪ ዊሊያምስና ባለቤቷ ላሪ ዊሊያምስ የ37 ዓመትና የ29 አመት ጽኑ እስራት የተወሰነባቸው ሲሆን በሲያትል አካባቢ የሚኖሩ ትዮጵያዊያን በፍርዱ መደሰታቸውን በተለይ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሰሜን ዕዝና የአየር ኃይል ዋና አዛዦች በሌሎች ተተኩ

የፓርላማው አባል የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕግ አማካሪ ሆኑ

በዮሐንስ አንበርብር

(ሪፖርተር ረቡዕ ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም. Oct. 30, 2013)፦ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቅራቢነትና በፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ አማካይነት የጄኔራል መኮንኖች ሹመት ከተካሄደ በኋላ፣ በመከላከያ ሠራዊቱ አመራሮች ላይ የኃላፊነት ሽግሽግ ተካሄደ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ