አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተላልፈው ተሰጡ

“የተፈጠረው ሁናቴ እጅግ ቢያሳዝንም ይህንን አለማቀፍ ህግ የሚጥስ አገዛዝ ለመጣል ሁላችንም ቆርጠን እንድንነሳ ያደርጋል” አቶ ነአምን ዘለቀ

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. July 3, 2014)፦ ከዱባይ ወደ አስመራ በመጓዝ ላይ የነበሩትና የመን ውስጥ ሰንዓ ከተማ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለትራንዚት የወረዱት የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እዛው የመን ታግተው ከቆዩ በኋላ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው መሰጠታቸው ተረጋገጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን እገታ መፍትሄ አላገኘም

ወደ ኢትዮጵያ እንዳይተላለፉ ስጋቱ አይሏል

“ኤርትራዊያኖች የየመን አየር መንገድን እንዳይጠቀሙ ማስተባበር ያስፈልጋል” አቶ ዳንኤል ጥላሁን (የህግ ባለሙያ)

Ethiopia Zare (ሐሙስ ሰኔ 26 ቀን 2006 ዓ.ም. July 3, 2014)፦ የግንቦት ሰባት ንቅናቄ ዋና ጸሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ለጉዞ መሸጋገሪያ የመን ከገቡ ጀምሮ በአገሪቱ ደህንነቶች ታፍነው መወሰዳቸውን አስመልክቶ ኢትዮጵያዊያን ቁጣቸውን እያሰሙ ሲሆን በተለይ የየመን አየር መንገድን በመቃወም ኤርትራዊያን የጉዞ ማእቀብ እንዲያደርጉ አንድ ተቀማጭነቱን ካናዳ ያደረገ የህግ ባለሙያ ጥሪ አቀረበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቫንኩቨር የኢ/ኦ/ተ ምእመናን እንባችን ታበሰ አሉ

"የጳጳሳት ስራ ሕዝብን ማጽናናት እንጂ ህዝብን ማሳዘን አይደለም" አቡነ መቃርዮስ (ሊቀጳጳስ)
"እረኛው በጎቹን መፈለግ ትቶ በጎቹ እረኛውን የሚፈልጉበት ግዜ መጣ" አቶ አስራት ተሾመ (የሰበካ ጉባኤው ሊቀመንበር)
የቫንኩቨርና አካባቢው ምእመናን

ለላፉት ሶስት አመታት በተለያዩ አለመግብባቶች ሲጓተት የነበረው የቫንኩቨር ጼዴንአ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት በአቡነ መቃርዮስ፤ ሊቀጳጳስ ባራኪነት ተከበረ፤ የቫንኩቨር ምእመናን የደስታ እንባ አነቡ። ባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ በተከበረው በዓል ላይ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቫንኩቨርና አካባቢው ምእመናን፤ ከአመታት ልፋትና ጸሎት በኋላ ሀሳባቸው ሰምሮ የመድሄኔዓለምና የቅድስት ማርያም ጽላት ስለገቡላቸው ደስታቸውን በዝማሬና በእንባ ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ ለሃዋርያዊ አገልግሎት ወደ ቫንኩቨር አቀኑ

ብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ Abune MekariosEthiopia Zare (አርብ ሰኔ 20 ቀን 2006 ዓ.ም. June 27, 2014)፦ በቫንኩቨር ካናዳ የምትገኘውን የጼዴነያ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት የሚከብርበትንና ታቦተ ህጉን ከመንበሩ ለማስገባት ወደ አካባቢው ሀዋርያዊ ጉዞ የሚያደርጉት ብጹእ አቡነ መቃርዮስ ነገ በስፍራው የወንጌል ትምህርት እንደሚሰጡ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እሁድን በአራዳ ምድብ ችሎት

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ለዛሬ የተቀጠሩትን ሦስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች አቤል ዋበላ፣ በፍቃዱ ኃይሉና ማኅሌት ፋንታሁን መዝገብ ለማየት የተሰየመው የተጠርጣሪዎቹ ቤተሰቦች ችሎት ሳይገቡ ነበር። ከመጀመሪያው ችሎት በኋላ ችሎቱ ባለው ቦታ ልክ ቤተሰብ እንዲገባ ተፈቅዶ የነበረ ቢኾንም ዳኛዋ የዕለቱን ሥራ ሲጀምሩ ስለዚህ ጉዳይ የሚያውት ነገር ያለ አይመስልም። ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ የሚሰየሙት ዳኞች ተረኛ ዳኞች በመኾናቸው የዛሬዋ ዳኛም ለመዝገቡና ለጉዳዩ አዲስ ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቅዳሜን በአራዳ ምድብ ችሎት

Journalist Tsion Girma, ጋዜጠኛ ጽዮን ግርማ
ጽዮን ግርማ
This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ቀኑ ቅዳሜ በመኾኑ ፒያሳ በሚገኘው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ግቢ ውስጥ ከዘጠኙ ተጠርጣሪ ቤተሰቦች ውጪ መደበኛ ችሎት ሊከታተል የመጣ ሌላ ሰው አልነበረም። ከሁለት ሰአት ተኩል ጀምሮ ሲጠራቀም የቆየው የችሎት ተከታታይ ቀስ በቀስ በርከት ብሎ በግቢው መታየት ጀመረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጫት ኮንትሮባንድ በስዊድን ክብረወሰን ሰበረ

ጫቱን ሲያስገቡ የተያዙት የሦስት ዓመት እስራት ይጥብቃቸዋል
በሕገወጥ መንገድ ከሎንዶን ወደ ስዊድን ሲግባ የተያዘ ጫት Chat, Foto: Scanpix

Ethiopia Zare (ዓርብ ግንቦት 1 ቀን 2006 ዓ.ም. May 9, 2014)፦ 816 ኪሎ ጫት ከሎንዶን በስዊድንዋ የወደብ ከተማ ጉተምበርግ በኩል በመርከብ ተጭኖ ሲገባ አፕሪል ላይ መያዙንና ሁለት ሰዎችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሜትሮ ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ አስነብቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት አንድነት የጠራውን የሰላማዊ ሰልፍ እንደሚቀላቀሉ አስታወቁ

በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች ታስረው የሰነበቱትና ቀሪዎቹ የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ዛሬ ባደረጉት ሳምንታዊ የወጣቶች የውይይት ፕሮግራም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ (አንድነት) የ"እሪታ ቀን" በሚል የጠራውን ሰልፍ በግንባር ቀደምነት በመቀላቀል ድምጻቸውን እንደሚያሰሙ አስታውቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አገር እንዲህ ኾናም አትቀርም (ሊያነቡት የሚገባ)

ጽዮን ግርማ - አዲስ አበባ


ዘወትር እንደምታደርገው ሁሉ በምታዝበት ሬዲዮ ጣቢያ ጓደኞቿን ሰብስባ ወደ ስቱዲዮ የገባችው ሚሚ ስብሃቱ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ስለታሠሩት ሁለት ጋዜጠኞችና ሰባት ጦማሪዎች ከፖሊስ አገኘኹት ያለችውን መረጃ ጠቅሳ ስታወራ ነበር። ኢትዮጵያን ለማተራመስ ከሚሠራው አርቲክል ዐሥራ ዘጠኝ ከሚባል ድርጅት ጋር ሲሠሩ ነበር፣ትልልቅ ሆቴል እየተገናኙ ይወያዩ ነበር፣ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎችን ያደራጁ ነበር፣ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅትና ከአምነስቲ እንዲሁም ከግብጽና ከኤርትራ ገንዘብ ይቀበሉ ነበር፤ የሚሉ ውርጅብኞችን በማውረድ እነርሱን የኢትዮጵያ ጠላት እራሷን ደግሞ የኢትዮጵያ ወዳጅ አድርጋ በመሳል ውንጀላዋን ስታዥጎደጉደው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ