ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ሕዝቡ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጋር እንዲኾን ጠየቁ

L. Gen. Bacha Debele

ሠራዊቱ ማጥቃት እንዳለበት ወስኖ እየሠራበትም ነው ብለዋል

ኢዛ (ረቡዕ ሐምሌ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 14, 2021)፦ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ከዚህ ቀደሙ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጐን እንዲቆም የአገር መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ሥራዎች ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ገለጹ። ጁንታው ትንኮሳውን መቀጠሉንም ሌ/ጄኔራሉ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማምሻውን በሰጡት ተጨማሪ መረጃ፤ ሕዝቡ መገንዘብ አለበት ብለው የገለጹት ደግሞ ወታደራዊ ሥራ በወታደር እንጂ በአክቲቪስቶች የሚከናወን አለመኾኑን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጸጥታ ኃይሉ ወደ ማጥቃት እንዲሸጋገር የአማራ ክልል ትእዛዝ ሰጠ

ግዛቸው ሙሉነህ

“የተከፈተብን መጠነ ሰፊ ወረራ የሕልውና ጉዳይ በመኾኑ የክልሉ መንግሥት የትኛውንም ዐይነት አፍራሽ ግብ ያላቸውን አካላት እኩይ ሴራ አይታገስም” የአማራ ክልል መንግሥት

ኢዛ (ረቡዕ ሐምሌ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 14, 2021)፦ የሕወሓት የሽብር ቡድን በተከፈተበት ይፋዊ ጦርነት ራሱን ከመከላከል ወጥቶ ወደ ማጥቃት ለመሸጋገር መወሰኑን የአማራ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጁንታው የኢትዮጵያ ሕልውና ቀንደኛ ጠላት መኾኑን ገለጹ

PM Abiy Ahmed

“ጁንታው ሕፃናትና ወጣቶችን በአደንዛዥ ዕጽ እያሳበደ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛል” ዶ/ር ዐቢይ

ኢዛ (ረቡዕ ሐምሌ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 14, 2021)፦ “ጁንታው የኢትዮጵያ ሕልውና ቀንደኛ ጠላት መኾኑን ደግሞ እያስመሰከረ ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ አስታወቁ። ጁንታው ሕፃናትና ወጣቶችን በአደንዛዥ ዕጽ እያሳበደ ወደ ጦርነት እየማገደ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለአዲስ አበባ ከተማ ለ2014 በጀት 70.6 ቢሊዮን ብር አጸደቀ

Office of the Mayor Addis Ababa

ከ2013 በጀት ዓመት አንጻር ሲታይ የ15 በመቶ ብልጫ ያለው ነው

ኢዛ (ማክሰኞ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 13, 2021)፦ ተሰናባቹ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ለ2014 በጀት ዓመት 70.07 (ሰባ ነጥብ ዜሮ ሰባት) ቢሊዮን ብር በጀት በማጽደቅ የሥራ ጊዜውን አጠናቀቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአውሮፓ ሕብረት ውሳኔን ኢትዮጵያ ተቃወመች

European Union Flag

በትግራይ የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ እየተካሔደ ባለው የማጣራት ሒደት ላይ ሕብረቱ ጣልቃ ገብ መኾኑን ተገልጿል

ኢዛ (ማክሰኞ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 13, 2021)፦ በትግራይ የሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ የአውሮፓ ሕብረት አሳለፈ የተባለው ውሳኔ እየተካሔደ ባለው የማጣራት ሒደት ላይ ጣልቃ መግባት መኾኑን በመግለጽ የአውሮፓ ሕብረትን ውሳኔ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚያሳዝን ብሎታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሽብር የተፈረጀው ሕወሓት መሠረተ ሰፊ ወረራና ጥቃት ማድረግ መጀመሩን የአማራ ክልል አስታወቀ

TPLF

ወረራውን ለመቀልበስ ጥሪ ተላልፏል

ኢዛ (ማክሰኞ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 13, 2021)፦ በሽብርተኝነት የተፈረጀው የሕወሓት ቡድን የኢትዮጵያ መንግሥት በአንድ ወገን የወሰደውን የተኩስ አቁም ውሳኔ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም፤ በኢትዮጵያና በአማራ ሕዝብ ላይ መሠረተ ሰፊ የኾነ ወረራና ወታደራዊ ጥቃት ማድረግ መጀመሩን የአማራ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሽብር የተፈረጀው ቡድንና በአዲስ አበባ እየተወሰደ ያለው እርምጃ

Harmony Hotel, Addis Ababa

ለሁለት ቀን ተዘግተው የነበሩ ሆቴሎችና የምሽት ክለቦች ወደ ሥራ ተመልሰዋል

ኢዛ (ማክሰኞ ሐምሌ ፮ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 13, 2021)፦ በሽብርተኝነት የተፈረጀው የሕወሓት ቡድን በመደገፍ በአዲስ አበባ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ሲያደርጉ ነበሩ የተባሉ የትግራይ ክልል ተወላጆች በጸጥታ አካላት ተይዘው እየታሰሩ መኾኑ እየተገለጸ ነው። በአንዳንድ አካባቢዎች ለሁለት ቀን ተዘግተው የነበሩ ሆቴሎችና የምሽት ክለቦች ወደ ሥራ ተመልሰዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኤርትራ የሕወሓት ቡድን የኤርትራ ስደተኞችን እየጨፈጨፈ ነው አለች

የማነ ገብረመስቀል

በጄኔቭ የኤርትራ ኤምባሲ በጉዳዮ ላይ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር እየተነጋገረበት ነው

ኢዛ (ሰኞ ሐምሌ ፭ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 12, 2021)፦ በሽብርተኝነት የተፈረጀው ሕወሓት ቡድን በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የበቀል እርምጃ እየወሰደ መኾኑን ኤርትራ ገለጸች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የክልል ምክር ቤት የምርጫ ውጤት

Prosperity Party

ምርጫ በተካሔደባቸው በሁሉም ክልሎች ብልጽግና አሸናፊ ኾኗል

ኢዛ (እሁድ ሐምሌ ፬ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 11, 2021)፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ 2013 ተከትሎ ይፋ ባደረገው ውጤት መሠረት ለክልል ምክር ቤት በተደረገው ምርጫ አኛናፊ ፓርቲዎችን አሳውቋል። ለክልል ምክር ቤቶች በተደረገው ምርጫም ብልጽግና ፓርቲ አሸናፊ መኾኑን የሚያመለክት ኾኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብልጽግና አሸናፊ መኾኑ ተረጋገጠ

Ethiopian Election 2021 result

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 410 ወንበሮችን አሸንፏል
ኢዜማ አራት፣ አብን አምስት፣ ጌሕዴፓ ሁለት ወንበሮች አግኝተዋል

ኢዛ (ቅዳሜ ሐምሌ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 10, 2021)፦ በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ የኾነ የምርጫ ውጤቱን ያስታወቀ ሲሆን፤ በሁሉም የምርጫ ክልሎች ብልጽግና ፕርቲ አሸናፊ መኾኑን አረጋግጧል። ብልጽግና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 410 ወንበሮች አግኝቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!