የጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ነገ ይመክራል ተብሎ እየተጠበቀ ነው

Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)

የዐረብ ሊግ አገራት ጣልቃ ገብነትን ኢትዮጵያ አውግዛለች

ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፴ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 7, 2021)፦ ኢትዮጵያ የታላቁን ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ የውኃ ሙሌት መጀመሯ በተሰማ ማግሥት የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ነገ ሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም. ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለትግራይ ለ2014 የተያዘው በጀት በእንጥልጥል ላይ ነው

Ahmed Shide, Minster of Finance

መንግሥት በጀቱ እንዲለቀቅ ውሳኔ ላይ አልደረሰም
ለክልሉ 12 ቢሊዮን ብር በጀት ተመድቦለት ነበር

ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፴ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 7, 2021)፦ የፌዴራል መንግሥት በ2014 በጀት ዓመት ለትግራይ ክልል ተብሎ የተያዘውን በጀት ለመልቀቅ ውሳኔ ላይ አለመድረሱ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዋሽ ባንክ በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት 5.58 ቢሊዮን ብር አተረፈ

Awash Bank

ከ100 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ሒሳብ መጠን በማስመዝገብ በግል ባንኮች ታሪክ አስመዘገበ

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 6, 2021)፦ በተጠናቀቀው የ2013 ዓ.ም. በጀት ዓመት አምስት ነጥብ አምስት ስምንት (5.58) ቢሊዮን ብር ማትረፉን አዋሽ ባንክ በዛሬው ዕለት አስታወቀ። ከግል ባንኮች የተጠናቀቀውን የሒሳብ ዓመት ሪፖርት በማቅረብ ሁለተኛው የግል ባንክ ኾኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ የውኃ ሙሌት ጅማሮ

Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD)

ኢትዮጵያ በአቋሟ ጸንታ ቅጥላለች

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 6, 2021)፦ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት መጀመሩ እየተነገረ ነው። የግብጽ የመስኖ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ለግብጽ መገናኛ ብዙኃን እንደገለጸው ከኾነ፤ ኢትዮጵያ ለግብጽ በኦፊሴል ሁለተኛውን ዙር የውኃ ሙሌት መሙላት መጀመርዋን አስታውቃላች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በባሕር ዳር ከተማ የአብኑ እጩ ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ አሸናፊ መኾናቸው ተረጋገጠ

Dr. Desalegne Chane

47,083 ድምፅ አግኝተው ነው ያሸነፉት

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 5, 2021)፦ በአማራ ክልል በባሕር ዳር ከተማ የምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደሩት የአብን ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ አሸናፊ መኾናቸውን ምርጫ ቦርድ አረጋገጠ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ ጉዳይና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የፓርላማ ማብራሪያ

PM Abiy Ahmed

“ጁንታው የሚሰጠውን በጀት ከመከላከያ እኩል የኾነ ኃይል ለመገንባት አውሎታል” ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ
ኢትዮጵያ ላይ ግልጽ አደጋ ካልመጣ በስተቀር ከማንም ጋር ግጭት ውስጥ አንገባም

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 5, 2021)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከምክር ቤቱ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያና ምላሽ ሰጥተዋል። ዛሬ ሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ የተሰጠባቸው ጉዳዮች ተጠባቂ የነበረው የትግራይ ክልልና የተኩስ አቁም አዋጅን ጨምሮ በሌሎች ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ነበሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአብን መግለጫ፤ የትሕነግ ማንሰራራት የደኅንነታችን አደጋ ነው

National Movement of Amhara (NAMA)

የአገርን ደኅንነት ለመጠበቅና የሚፈለግበትን ለማድረግ ቁርጠኛ መኾኑንም ገልጿል

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 5, 2021)፦ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በአገራችን ላይ የተደቀነውን ጽኑ የብሔራዊ ደኅንነት ሥጋት ለመመክትና ከምንም በላይ የሕዝብ ጥቅምና ክብር፤ እንዲሁም የአገረ መንግሥቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ድርጅታዊ አስተዋጽኦ ለማድረግ ቁርጠኛ ነኝ አለ። የትሕነግ ማንሰራራት የደኅንነት ሥጋት መኾኑንም ገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዶ/ር ዐቢይ አሸናፊ የኾኑበት የተረጋገጠው የምርጫ ውጤት ይፋ ኾነ

PM Abiy Ahmed Election 2021 result

76,892 ድምፅ አግኝተዋል
ተፎካካሪያቸው ያገኙት ድምፅ 236 ነው

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 5, 2021)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአሁኑ ወቅት የተረጋገጡ የምርጫ 2013 ውጤቶችን ይፋ እያደረገ ሲሆን፤ ዛሬ ይፋ ካደረጋቸው የተረጋገጡ የምርጫ ውጤቶች መካከል ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አሸናፊ የኾኑበትን የምርጫ ውጤት አስታውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በትግራይ ከፍተኛ የሰብአዊ ቀውስ ይፈጠራል ተብሎ ተሰግቷል

State of Emergency Fact Checking

የሕወሓት የሽብር ቡድን በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ገብቶ ግድያዎች እየፈጸመ ነው

ኢዛ (እሁድ ሰኔ ፳፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. July 4, 2021)፦ በሽብርተኝነት የተፈረጀው የሕወሓት ቡድን የኢትዮጵያ መንግሥት የተናጠል (የአንድ ወገን) የተኩስ አቁም እወጃ ካደረገ በኋላ ወደ መቀሌ እና ሌሎች የክልሉ ከተሞች በመግባት በነዋሪዎች ላይ ጥቃት እየፈጸመ መኾኑን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!