የሕወሓትን የጁንታ ቡድን አመራሮች ለሚጠቁም 10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተዘጋጀ

ሌተናል ጄኔራል አስራት ዴኔሮ

የጠቋሚዎች ማንነት የማይገለጽና በምስጢር እንደሚያዝ ተገልጿል

ኢዛ (ዓርብ ታኅሣሥ ፱ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 18, 2020)፦ የሕወሓት ጁንታ አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ ማንኛውም ዜጋ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት የሚሰጥ መኾኑን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮ ሱዳን ድንበር የተከሰተውን በቅርብ እየተከታተሉ መኾኑን ገለጹ

PM Abiy Ahmed's Twitter page

“የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ትስስር ያልተረዱ ናቸው ጉዳዩን የሚያራግቡት” ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ኢዛ (ሐሙስ ታኅሣሥ ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 17, 2020)፦ ሰሞኑን በኢትዮ ሱዳን ድንበር አካባቢ ግጭት መከሰቱን የሚያመለክቱ መረጃዎች ሲወጡ የነበረ ሲሆን፤ ዛሬ ማምሻውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በትዊተር ገጻቸው በድንበሩ አካባቢ ከሚሊሻ ጋር የተፈጠረውን ክስተት መንግሥት በቅርበት እየተከታተለው መኾኑን ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእነጃዋር መሐመድ ችሎት ይቀየርልን ጥያቄ ውድቅ ኾነ

Jawar Mohammed (L), Bekele Gerba (R)

ፍርድ ቤት አንቀርብም ካሉ በፖሊስ ተገደው ይቅረቡ ተብሏል

ኢዛ (ሐሙስ ታኅሣሥ ፰ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 17, 2020)፦ ለደኅንነታችን እንሰጋለን በሚል በእስር ከሚገኙበት ማረሚያ ቤት በቅርብ በሚገኝ ችሎት ጉዳያችን ይታይ የሚል አቤቱታ ያቀረቡትን የእነጃዋር መሐመድን አቤቱታ የተመለከተው ፍርድ ቤት ጥያቄያቸውን ውድቅ አድርጎታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ ውል አገልግሎት ዳግም ጀመረ

Ethiopian Federal Documents Authentication and Registration Agency

የንብረት ሽያጭ ክፍያዎች የባንክ ደረሰኝ ይጠየቅባቸዋል

ኢዛ (ረቡዕ ታኅሣሥ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 16, 2020)፦ ከብር ኖት ቅያሬው ጋር ተያይዞ ተቋርጦ የነበረውን ንብረትን በስጦታ የማስተላለፍ የውል አገልግሎት እንደተጀመረ ተገለጸ። የሚንቀሳቀስም ኾነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ በባንክ በኩል የሚፈጸም እንደሚኾን ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጓድ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ የቀብር ሥነሥርዓት ተፈጸመ

Fikreselassie Wogderess

የመጀመሪያው የኢሕዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ነበሩ

ኢዛ (ረቡዕ ታኅሣሥ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 16, 2020)፦ ታኅሣሥ 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ዜና እረፍታቸው የተሰማው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ታኅሣሥ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዲስ አበባ መንበረ ጽባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጉምቱው የኪነጥበብ ባለሙያ ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ አረፈ

Tesfaye Gessesse

በኢትዮጵያ የኪነጥበብ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ አበርክቷል

ኢዛ (ረቡዕ ታኅሣሥ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 16, 2020)፦ አንጋፋው የኪነጥበብ ባለሙያና መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ በ83 ዓመቱ ዛሬ ታኅሣሥ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስለአዲስ አበባ የሚሰማው ጉድ ቀጥሏል

Addis Ababa

የተሰረቀው መሬት ከ13 ነጥብ 6 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ ኾኗል
በሕገወጥ መንገድ በተመሠረቱ 64 መንደሮች 6 ነጥብ 8 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ተይዟል

ኢዛ (ረቡዕ ታኅሣሥ ፯ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 16, 2020)፦ በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መንገድ የተወረረውን መሬት ከሥር ከሥር በሚደረግ ማጣራት እየተገኘ ያለው መረጃ የከፋ ደረጃ ላይ ስለመድረሱ እየተመላከተ ሲሆን፤ ዛሬ ይፋ በተደረገው መረጃም በሕገወጥ መንገድ የተያዘው መሬት ከ13 ነጥብ 6 ሚሊዮን ካሬ ሜትር በላይ ደርሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የትግራይ ጊዜያዊ ካቢኔ ነገ ሥራ ይጀምራል

Mulu Nega

የመንግሥት ሠራተኞች ሰኞ ሥራ እንዲጀምሩ ጥሪ ተደርጓል
በሥራ ገበታው ላይ ያልተገኘ በፈቃዱ እንደለቀቀ ይቆጠራል

ኢዛ (ቅዳሜ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 12, 2020)፦ የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድረው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ከነገ ታኅሣሥ 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ሥራ እንደሚገባና ከታኅሣሥ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. በሥራ ገበታው ላይ የማይገኝ ሠራተኛ በገዛ ፈቃዱ ሥራውን እንደለቀቀ የሚቆጠር መኾኑን ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ጓድ ፍቅረሥላሴ አረፉ

Fikreselassie Wogderess and Genet Ayele

"ምን ከእንግዲህ ወዲያ የኢትዮጵያን ጠላቶች መጨረሻ ዓየን አይደል እንዴ?” ጓድ ፍቅረሥላሴ በመጨረሻ ሰዓታቸው የተናገሩት

ኢዛ (ቅዳሜ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 12, 2020)፦ በደርግ የአገዛዝ ዘመን ለዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትር በመኾን ሲያገለግሉ የነበሩት ጓድ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ማረፋቸው ተሰማ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ተደፍሯል

National Election Board of Ethiopia (NEBE)

የክልሉ ፖሊስ በዋና መሥሪያ ቤቱ ሊፈጸም የነበረውን የእስር ሙከራ አወገዘ

ኢዛ (ቅዳሜ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፳፻፲፫ ዓ.ም. December 12, 2020)፦ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በዋና መሥሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የፖለቲካ ድርጅት አመራር አባላትን የቤንሻንጉል ክልል ፖሊስ ለማሰር ያደረገውን ሙከራ የቦርዱን ሕገ መንግሥታዊ ኃላፊነት እንደሚጋፋና የድርጊቱን አሳሳቢነት አስታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ