ኹከቱ በተለያዩ ከተሞች ያደረሰው ጉዳት እና መንግሥት

Hachalu Hundessa

ከአንድ ሺህ አራት መቶ በላይ ተጠርጣሪዎች ታስረዋል

ኢዛ (እሁድ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 5, 2020)፦ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በአዲስ አበባና በተለያዩ የኦሮሚያ ክልሎች ከፍተኛ ኹከት ከመከሰቱ ባሻገር የበርካቶች ንጹኀን ዜጎችና የመንግሥት የጸጥታ አስከባሪ አባላት ሕይወት ከመጥፋቱም በላይ ለጊዜው በውል ያልታወቀ ንብረት መውደሙ ይታወቃል። በአሁኑ ወቅት የመከላከይ ኃይል፣ የልዩ ኃይልና የፖሊስ ኃይሎች ከሕብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ኹከቱ በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ሰላም በማስፈን ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ፍርድ ቤት ቀረቡ

Jawar Mohammed (L), Bekele Gerba (M) and Hachalu Hundessa (R)

በኹከቱ 78 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል

ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 2, 2020)፦ አቶ ጃዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ለበርካቶች ሞት ምክንያት የኾነውን ኹከት በመቀስቀስ እና በሰው ሕይወት ማጥፋት ተጠርጥረው ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ሥርዓተ ቀብር ዛሬ ተፈጸመ

Hachalu Hundessa's funeral, 2nd July 2020

የቀብር ሥነ ሥርዓቱ የተፈጸመው በአምቦ ነው

ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 2, 2020)፦ ባለፈው ሰኞ በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ ያለፈው የታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. በተወለደበት አምቦ ከተማ በሚገኘው ገዳመ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያ ተፈጸመ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአርቲስት ሐጫሉ ግድያ ተጠርጥረው የተያዙ ሦስት ሰዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ

Hachalu Hundessa

ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ ሴት ነች

ኢዛ (ሐሙስ ሰኔ ፳፭ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 2, 2020)፦ በአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥረው የተያዙት ሦስት ሰዎች ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ከተጠርጣሪዎቹ አንዷ ሴት ነች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እስክንድር ነጋ ታሰረ

Eskinder Nega

“በቁጥጥር ሥር የዋለው በአዲስ አበባ ኹከትና ግጭት እንዲፈጠር በመቀስቀስ ተጠርጥሮ” ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ

ኢዛ (ረቡዕ ሰኔ ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 1, 2020)፦ የአርቲትስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በአዲስ አበባና በተለይም በኦሮሚያ ክልል በርካቶች እየታሰሩ ሲሆን፣ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 24 ቀን በአዲስ አበባ ከታሰሩት ውስጥ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ መታሰሩ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 42ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 42nd, 2012 Ethiopian calendar

የዓመቱ አርባ ሁለተኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከሰኔ 15 - 21 ቀን 2012 ዓ.ም.) ሳምንት የአገሪቱ መሪ አጀንዳ ኾኖ የሰነበተው የህዳሴ ግድብና ከዚሁ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ከአገር አልፎ የዓለምን ዓይንና ጆሮ የያዘ ነበር ማለት ይቻላል። ኢትዮጵያ የግድቡን የውኃ ሙሌት ለመጀመር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ባለችበት ወቅት በሦስቱ የተፋሰሱ አገራት መሪዎች በአፍሪካ ሕብረት በኩል እንዲሸማገሉ ግብጽ ፍቃደኛ መኾንዋን ማሳወቋና ብዙም የተጠበቀ አልነበረም። ኾኖም ግብጽ ወደ ዳር ስትገፋው የነበረው የአፍሪካ ሕብረትን አወያይነት ተቀብላ ውይይት መደረጉ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው የሳምንቱን ዜና ኾኖ ታይቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 35 ሰዎች ታሰሩ

Jawar Mohammed and Hachalu Hundessa

“የአርቲስት ሐጫሉ ግድያ የተቀነባበረ ሴራና ሥልጣን በአቋራጭ ለማግኘት የታቀደ ነው” አቶ ሽመልስ

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፳፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 30, 2020)፦ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተቀነባበረ ሴራ መኾኑንና ሥልጣን በአቋራጭ ለማግኘት ያቀዱ ኃይሎች የፈጸሙት ድርጊት መኾኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ገለጹ። ፖሊስ በበኩሉ አቶ ጃዋር መሐመድን ጨምሮ 35 ሰዎች መታሰራቸውን ገልጿል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአርቲስት ሐጫሉን ግድያ ተከትሎ በአገሪቱ በርካቶች ተገደሉ፣ ከፍተኛ ንብረት ወደመ

Hachalu Hundessa

በሐረር የራስ መኮንን፣ በሎንዶን የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሐውልቶች ፈርሰው ተሰባበሩ

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፳፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 30, 2020)፦ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከትናንትና ምሽት ጀምሮ በተለይ በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ተረብሸው ያደሩ ሲሆን፣ ንጋት ላይ ደግሞ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በርካታ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተነገረ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ታዋቂው አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ አለፈ

Hachalu Hundessa

ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፳፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. June 30, 2020)፦ ታዋቂው የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ትናንት ሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰበት ጥይት መገደሉ ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2012 ዓ.ም. 41ኛ ሳምንት አንኳር ወሬዎች

Ethiopia Zare's weekly news digest, week 41th, 2012 Ethiopian calendar

የዓመቱ አርባ አንደኛ ሳምንት አንኳር ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ክንውኖች

ኢዛ (ከሰኔ 8 - 14 ቀን 2012 ዓ.ም.) ያሳለፍነው ሳምንት መሪ አጀንዳ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ በተያዩ አቅጣጫዎች የተዘገቡ ዜናዎች ናቸው። በኢትዮጵያ በግብጽና በሱዳን መካከል እየተደረገ የነበረው ውይይት በውጤት ባይቋጭም ውይይቱን አስመለክቶ በየዕለቱ የተሰጡ መረጃዎች ያዝ ለቀቅ ያሉ ኾነው ከቆዩ በኋላ ግብጽ ውይይቱን ችላ ብላ ደግሞ ወደተባበሩት መንግሥታት አቤት ያለችበት ኾኗል። ከኢትዮጵያ አንፃር ድርድሩ ውጤት አመጣ አላመጣ፤ እኔ በያዝኩት ዕቅድ መሠረት በቀጣዩ ወር የውኃ ሙሌት ሥራዬን አከናውናለሁ ብላ ቁርጥ ያለ ምላሽ ሰጥታለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ