የእነአቶ ጃዋር መሐመድና የቅርብ ቤተሰቦች የባንክ አካውንት ታገደ

Jawar Mohammed (L) and Bekele Gerba (M)

“አካውንቶቹ የታገዱት በሕጋዊ መንገድ ነው” ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ

ኢዛ (ዓርብ ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 31, 2020)፦ ከአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በቅርቡ በተፈጠረው ቀውስ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት የእነአቶ ጃዋር መሐመድ የባንክ አካውንት መታገዱ ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአንድ ቀን 915 በኮሮና የተጠቁ ሰዎች ተገኙ

Total coronavirus cases in Ethiopia, June 31, 2020

የተጠቂዎች ቁጥር 17,530፣ የሟቾች ቁጥር 274 ደርሷል

ኢዛ (ዓርብ ሐምሌ ፳፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 31, 2020)፦ ካለፉት ሦስት ሳምንታት ወዲህ ከቀድሞው በተለየ በየዕለቱ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣት፤ በዛሬው ዕለት 915 የሚኾኑ አዳዲስ ተጠቂዎች መገኘታቸው ታወቀ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“በአገሪቱ ለታየው ሥራአት አልበኝነትና ሽብርተኝነት ተጠያቂዎቹ የመንግሥት ባለሥልጣናት ናቸው” ባልደራስ

ባልደራስ እስክንድር ነጋ

ለደረሰው እልቂትና ንብረት ውድመት የአንድ ቀን ጀንበር የወለደው ችግር አይደለም

ኢዛ (ሐሙስ ሐምሌ ፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 9, 2020)፦ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕሬዝዳንት እስክንድር ነጋ እና አመራሮችን መታሰር ተከትሎ ፓርቲው ባወጣው መግለጫ፤ ሰሞኑን ጽንፈኞች በቀሰቀሱት አመጽ ለደረሰው እልቂትና ንብረት ውድመት የአንድ ቀን ጀንበር የወለደው ችግር አለመኾኑን ገለጸ። ፓርቲው የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በአገሪቱ እየታየ ለሚገኘው ሥርዓት አልበኝነትና ሲልም ሽብርተኛነት ቀጥተኛ ተጠያቂዎች እንደሆኑ አበክሮ እንደሚያምን በመግለጫው አሳውቋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሻሸመኔ ከንቲባን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ታሰሩ

Hachalu Hundessa

ኢንጂንየር ይልቃል ታስረው ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል

ኢዛ (ረቡዕ ሐምሌ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 8, 2020)፦ ለበርካቶች ሕይወት መጥፋት፣ መቁሰል፣ ግምቱ ለጊዜው ላልታወቀ በርካታ ንብረት መውደም ምክንያት ከኾነው ኹከት ጋር በተገናኘ ታዋቂ ሰዎች፣ የፖለቲካ አመራሮችና የመንግሥት ኃላፊዎች እየታሰሩ ይገኛሉ። የሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ተማም ሁሴን እና የከተማዋ አስተዳደርና የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ናደው አምቦ ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ በመኾናቸው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

167 ሰዎች ተገድለዋል፣ 229 ቆስለዋል

Ethiopian Federal Police Commission

ከ4,700 ሰዎች በላይ በቁጥጥር ሥር ውለዋል

ኢዛ (ረቡዕ ሐምሌ ፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 8, 2020)፦ ባለፈው ሳምንት ሰኞ ምሽት ላይ የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ፣ በአዲስ አበባ፣ በሐረርና ድሬዳዋ ተቀስቅሶ በነበረው ኹከት የተጠረጠሩና በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሰዎች ቁጥር ከ4,700 በላይ መድረሱ ተነገረ። የሟቾች ቁጥር 167 መድረሱን የፌዴራል ፖሊስ ገለጸ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ፓርላማ ይቀርባሉ

PM Abiy Ahmed

ይነሳሉ ተብለው ከሚጠበቁት ውስጥ የሰሞኑ ኹከት፣ የህዳሴው ግድብና የበጀት ጉዳዮች ናቸው

ኢዛ (ማክሰኞ ሰኔ ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 7, 2020)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማክሰኞ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጋር ተገናኝተው በበጀት ጉዳይ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ። በወቅታዊ ጉዳዮችና የአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በተከሰተው ኹከት፣ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ጋር በተያያዘም ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተገምቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሕወሓት የፓርቲ ምዝገባ ሰርቲፊኬ እንዲሰረዝ አብን ጠየቀ

 አብን

ጥያቄውን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አቅርቧል

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 6, 2020)፦ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዛሬ ሰኞ ሰኔ 29 ቀን በሊቀመንበሩ በአቶ በለጠ ሞላ አማካኝነት በሰጠው መግለጫ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለሕወሓት የሠጠውን የፓርቲ ምዝገባ ሰርቲፊኬት እንዲሰርዝ ጥያቄ አቀረበ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትግራይ ቲቪ እና ድምፂ ወያኔ ከሳተላይት ላይ ወረዱ

Tigray TV, DW and OMN

የሣተላይት ሥርጭታቸው የሚከፈለው ከሕዝብ ገንዘብ ነበር

ኢዛ (ሰኞ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 6, 2020)፦ ከአርቲስት ሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በተቀሰቀሰው ኹከትና የበርካቶችን ሕይወት ካጠፋው ጉዳይ ጋር ተያይዞ የትግራይ ቲቪ እና ድምፂ ወያኔ ከሳተላይት እንዲወርዱ መንግሥት ማድረጉ ታወቀ። በአገር ቤት ሥርጭታቸውን ለማቆም ተገድደዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የህዳሴ ግድቡን ጨርሰናል፤ ውኃ መሙላት ይጀመራል” ዶ/ር ኢንጂንየር ስለሺ በቀለ

Grand Ethiopian renaissance dam

አስራ አንድ ታዛቢዎች የሚገኙ ሲሆን፤ ደቡብ ሱዳን፣ ማሊ፣ ኮንጎና ኬንያ ይገኙበታል

ኢዛ (እሁድ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 5, 2020)፦ ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ውኃ ለመሙላት የሚያስችላትን ግንባታ መጨረስዋንና የውኃ መሙላት ሒደቱን እንደምትጀምር የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢንጂንየር ስለሺ በቀለ ገለጹ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ግብጽ ገቡ

President Isaias Afwerki (L) and President Abdel Fatah Al Sisi (R)

ቀዳሚ አጀንዳቸው በአፍሪካ ቀንድ በሚገኙ አጎራባች አገሮች ዙሪያ ነው

ኢዛ (እሁድ ሰኔ ፳፰ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. July 5, 2020)፦ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ዛሬ እሁድ ሰኔ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ወደ ግብጽ በመሔድ ከፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር ተገናኙ። በሁለቱ አገሮችና በአፍሪካ ቀንዱ በሚገኙ አጎራባች አገሮች ዙሪያ ይነጋገራሉ ተብሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ