የመንፈሣውያን ማኅበራት ሀገራዊ አስተዋፅዖ (ከጊዜው ይታየው)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ከጊዜው ይታየው

"ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክህነቱ ያገኘውን ቦታ፣ ያቀፋቸው አባላት ያላቸውን ሁሉን ዐቀፍ ዕውቀት፣ ያሰባሰበውን ብሔራዊ ተዋጽኦ፣ የዘረጋውን ዓለም አቀፋዊ መዋቅር ያህል በምሣሌነት ከላይ እንዳነሣናቸው ማኅበራት የጎላ ሀገራዊ አስተዋጽዖ አይታይበትም። ከኃይማኖት ክርክሮች፣ ከመጻሕፍት እና መዝሙሮች፣ ከጉባዔያት እና ስብሰባዎች ባለፈ ለሀገር ዕድገት እና ለህዝቡ ማኅበራዊ አገልግሎት መስፋፋት ብሎም ኅብረተሰቡን ለዕድገት በማነሣሣት ረገድ ዘገምተኛነት አስተውላለሁ።"

ከላይ ያለው "የመንፈሣውያን ማኅበራት ሀገራዊ አስተዋፅዖ" በሚል ርዕስ ጊዜው ይታየው ከፃፉት አስተያየት የተቀነጨበ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሙስና (ከፕ/ር ሰይድ ሐሰን)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

በመሪ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስና ፋይናንስ ዲፓርትመንት ውስጥ የኢኮኖሚ ፕሮፌሠር የሆኑት ዶ/ር ሰይድ ሐሰን "On the Menaing and Practical Implication of Corruption" በሚል ርዕስ ሙስንና አስመልክቶ በእንግሊዝኛ ያቀረቡት ጽሑፍ፣ ”የሙስና ትርጉም፤ ተዛማጅ ክስተቶቹና በሀገርና በህዝብ ላይ የሚያስከትላቸው ጠንቆች” በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ለአማርኛ አንባብያን እንደሚከተለው ቀርቧል። መልካም ንባብ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

S3457 እና HR2003 በተመለከተ (ከአማኑኤል ዘሰላም)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

S3457 እና HR2003 በተመለከተ - መስተዋል ያለበት የጋራ የዲፕሎማሲ ሥራ

ከአማኑኤል ዘሰላም This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

በቅድሚያ በሀገር ቤትና ከሀገር ውጭ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ሁሉ እንኳና ለአዲሱ ዓመት በሠላምና በጤና እግዚአብሔር አደረሳችሁ! አደረሰን! እላለሁ። «መጪው ዓመትም በታሪካችን አዲስ ምዕራፍ የሚጀመረበትና በአዲስ አመለካከት በጋራ ሀገራችን ኢትዮጵያ ካለችበት የድህነት አዘቅት ውስጥ የምናወጣበት ዓመት ያድርግልን!» እያልኩ ለአንባብያን ለማካፈል የፈለኳቸውንና ከውጭ ግንኙነት እና የዲፕሎማሲ ሥራ ጋራ የተገናኙ አንዳንድ ሃሳቦችን በትህትና ለማቅረብ እሞክራለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

2000 ዓ.ም. እንዴት አለፈ? (ከአዜብ ጌታቸው)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

የፖለቲካውን ውቅያኖስ ማን ቀዘፈ? ማን በማዕበል ተነደፈ?

ከአዜብ ጌታቸው (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

ከሁሉ አስቀድሜ በሀገር ቤትና በመላው ዓለም ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገደኖቼ በሙሉ ”እንኳን ከዘመን ወደ ዘመን በሠላም አሸጋገራችሁ!” የሚለው የመልካም ምኞት መልዕክቴ ይድረሳችሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዕርቀ ሠላም (ከዶ/ር ሽመልስ ተክለጻድቅ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ዕርቀ ሠላም ማን ይፈልጋል? ለምንስ ያስፈልገናል?

ከሽመልስ ተክለጻድቅ (ዶ/ር)

በተጣሉ ግለሰቦች፣ ወገኖች፣ ማኅበረሰቦች መካከል ከሠላም መለስተኛ በሆነ መልኩ በአሸናፊው ወገን ተጽዕኖና ፍላጎት ላይ የተመሠረተ መረጋጋት ሊፈጠር ይችላል። መረጋጋቱ ለረጅም ጊዜ ከቆየና የአሸናፊው እብሪት ከበረደ፣ ተሸናፊውም የደረሰበት የአካልም ሆነ የመንፈስ ቁስሉ ካገገመ ሠላሙ እየዳበረ መሄድ ይችላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያና ችጋር (ከፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም)

የአንባብያን ድምፅ: 1 / 5

Star ActiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

መንግሥት ባለበት ህዝብ በችጋር አይሞትም

መስፍን ወልደማርያም (ፕ/ር)

Prof. Mesfin Woldemariyamበ1930ዎቹ የኢጣልያ አገዛዝ ሊያበቃ ሲል፣ ክፉ ረሃብ በአዲስ አበባ ውስጥ እንደነበረ አስታውሳለሁ፤ ምናልባትም በገጠር የከፋና ወደ ችጋር የሚጠጋ ሳይሆን አልቀረም የሚል ግምት አለኝ፤ በአፄ ኃይለሥላሴ አገዛዝ ችጋርን በዓይኔ ያየሁበትና ቀምሼው ምንነቱን ያወቅሁበት ነበር። በዚህም ምክንያት ብዙ ተናግሬአለሁ፣ ብዙም ጽፌአለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለእነአባኪያ «የትራፊክ ደንብ» የተሰጠ ምላሽ (ከዳኛቸው ቢያድግልኝ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

«በኤርትራ በቀር ወደ ኢትዮጵያ ነፃነት የሚወስድ መንገድ የለም» ለሚለው የእነአባኪያ «የትራፊክ ደንብ» የተሰጠ ምላሽ

ከዳኛቸው ቢያድግልኝ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

Detourየጀመርነው ሃሳብን በነፃነት መግለጽ መቻል፣ መከባበር፣ እውቀትን ከፍ ከፍ ማድረግ ሊበረታታ ይገባል። አንዳችን የሌላኛችንን ሃሳብ ማክበር ስንችል እኛነታችንን ሳይሆን ሃሳባችንን እያብጠለጠልነውና እያብላላነው መሄድ ስንችል በአስመራ መንገድ ይሁን በቸርችል ጎዳና ብቻ ቤተመንግሥት ከች ማለታችን አይቀርም። ሁላችንም የምንተጋው ነፃነታችንን እንድናገኝ ነው። ባርነትን ለመምረጥ እሰጥ አገባው ባላስፈለገንም ነበር። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”የቅዱሳንን ዐጽመ-ርስት፤ ርኩሣን አይወስዱትም!” (ከገሞራው)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

(የማስጠንቀቂያ ጦማር፣ ቁጥር ፩)

ገሞራው - ዘስዊድን

ለማላከብርዎ ቀማተኛ ...

በዚህ ቀዳማዊ ደብዳቤዬ ላይ ብዙኃን ቁምነገሮችን ለማስፈር፣ እምብዛም አያመቸኝም። ሊመቸኝ ካልቻለበት ወይም ከማይችልበት ምክንያቶች ውስጥ ዓይነተኛውና ተቀዳሚው ስለርስዎ ስለቀማኛው ማንነት በዝርዝር ለማወቅ ባለመቻሌ ነው። ስለቤተሰብዎ መሠረት፣ ስለሶሻል ዕርከናዊ ደረጃዎ፣ ስለትምህርት ጣራዎ፣ ስለሥራ ክፍልዎ፣ ስለኑሮ ባህርይዎ፣ ... በዝርዝር ባውቅ ኖሮ፣ በሰፊው አሟልቼ እጅግ በሚያመረቃ አቀራረብ፣ በጽፍኩልዎ ነበር። የእርስዎን ገበናዊ ራዕይ በመላምት ጅምላዊ ትኩረት ሳይ ግን አንድ ነጥብ ፍንትው ብሎ በግልጽና በጉልህ ታይቶኛል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እናንት የዋሆች ከኤርትራ የኢትዮጵያን ነፃነት እንዴት ትሻላችሁ? (ከሙሉነህ ዮሐንስ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ሙሉነህ ዮሐንስ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ምላሽ “በኤርትራ በቀር ወደ ኢትዮጵያ ነፃነት የሚወስድ መንገድ የለም” በሚል አባኪያና ጓደኞቹ ለጻፉት

በመጀመሪያ ጓደኛየ አባኪያ ሠላም ላንተና ለጓደኞችህ ይሁን! ሰሞኑን ኢትዮጵያ ዛሬ (www.ethiopiazare.com) ድረ-ገጽ ላይ ያወጣችሁትን ጽሑፍ በግርምትና በአንክሮ ደጋግሜ አነበብኩት። ይህን እንደሳማ የሚቆጠቁጥ አርዕስት ደፍራችሁ ለውይይት ስላቀረባችሁት እያመሰገንኩ፤ አስተሳሰባችሁ ግን አስደንግጦኛል፤ አጥብቄም እቃወመዋለሁ። ኢትዮጵያውያን ወገኖች የኤርትራን ጉዳይ በዚህ መልኩ ያዩታል የሚል ግምት አልነበረኝም። አስተያየቴን በግል ልሰጣችሁ አስቤ ነበር። የጉዳዩን አደባባይ መውጣትና ለኢትዮጵያችን ሊኖረው የሚችለውን አደገኝነት ሳስበው እንዲሁም የውይይት ግብዣችሁን ሳክልበት በይፋ ምልከታየን ማድረስ መረጥኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከኤርትራ ጋር የመሥራት አስፈላጊነት (አባኪያና ጓደኞቹ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

በኤርትራ በቀር ወደ ኢትዮጵያ ነፃነት የሚወስድ መንገድ የለም

አባኪያና ጓደኞቹ ከካናዳ - ነኀሴ 2000 ዓ.ም.

ኤርትራን እንደ አገር፤ ሻዕቢያን እንደ አጋር

ብዙዎቻችሁ ይሄ ቀጥዬ የምጽፈው ነገር፤ ገና ከርዕሱ ወደላይ ሊላችሁ ይችላል። ለምደነዋል። ሃሳብን በነፃነት በመግለጽ መብት ብናምንም፣ ብዙ ራሳችንን እንደ ዲሞክራት የምንቆጥር ሰዎች በፖለቲካችን ውስጥ የሚሰነዘሩ አንዳንድ ሃሳቦች ሽቅብ ሽቅብ ሲሉን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ተመልክቻለሁ። ሃሳብ እንደተመልካቹ ነው። አንዳንድ ሰዎች የኤርትራ ነገር እይይይይይይ … ሊያሰኛቸው ይችላል። አንድ ምልከታ ነውና አልቃወምም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...