ትንሣኤሽ መቼ ነው?

ፊልጶስ - ከሆላንድ

 

በተንኮል ላይ ተንኮል፣ በክፋት ላይ ክፋት

 

በረሃብ ላይ ረሃብ፣ በስደት ላይ ስደት፤

 

በጦር ላይ ጦርነት፣ በውድመት ላይ ውድመት

 

 

በበደል ላይ በደል፣ በእስር ላይ እስራት፤

 

በጥል ላይ ጥላቻ፣ እርስ በርስ መባላት

 

ለነገ መደገስ ለጥፋት ለ’ልቂት፤ ...

 

ምነዋ ኢትዮጵያ … ትንሣኤሽ ራቀ ...

 

ትውልድ ሁሉ አለፈ በኑሮ እንደማቀቀ

 

የባዕድ እጅ እንዳየ እንደተሳቀቀ። …

 

ራዕይም አ’ተናል …

 

መሪና ተመሪ ሁሉም ተደናቁሯል፤

 

ህልማችንም ቃዥቷ፣ ተስፋችን ደብዝዧል

 

“ቀን እየጨለመ” ፅልመትን ተላብሷል

 

ትንሣኤሽ እንዴት ነው እስከመች ይቆያል?

 

--------//-------

 

ፊልጶስ - ከሆላንድ

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!