እህ ዛዲያማ! (ወለላዬ)
እህ ዛዲያማ! (PDF)
ከወለላዬ
በአንድ ጎጆ
እህ ዛዲያማ!
አንድ ቁርንጮ ይነጠፍና፣
ምርጫ በይፋ ይታወጅና
እህ ዛዲያማ!
እህ ዛዲያማ! ምን ልንገራችሁ፣
የደረሰውን ታውቁታላችሁ
ሕዝብ ጨብጦ ሙሉ ነፃነት፣
ያገር የመንግሥት ባለቤትነት፣
መያዝ ካልቻለ በነፃ ምርጫ፣
መቅመሱ አይቀርም እንደኛ ጡጫ
እህ ዛዲያማ!
እህ ዛዲያማ! ምን ልንገራችሁ፣
ያፍሪካን ምርጫ ታውቁታላችሁ
እዛ ኬንያ ጎረቤት ሀገር፣
በምርጫ ሰሞን አንዱ ሲናገር
ይሄ ፈጽሞ ኢትዮጵያ አይደለም፣
የህዝባችን ድምፅ ተሰርቆ አይቀርም
እንዳለው ሁሉ ህዝቡ በአንድነት
አርበድብዶታል ያለውን መንግሥት
እህ ዛዲያማ!
እህ ዛዲያማ! ምን ልንገራችሁ፣
የኛንም ጉዳይ ታውቁታላችሁ
እዛም ዚምባብዌ ምርጫ ተደርጎ፣
ድምፅ የሰጠውን ህዝብ ፈልጎ፣
ቆጠራ አጣርተው ባለመናገር፣
አፍነው ይዘው ፈጥረዋል ሽብር
እህ ዛዲያማ!
እህ ዛዲያማ! ምን ልንገራችሁ፣
ያፍሪካን ምርጫ ታውቁታላችሁ
ሌላም ጉድ አለ ሰሞኑን በግብጽ፣
ተቀናቃኙን በታቀበ ድምፅ፣
አፍኖ ይዞ እሱው ሊመረጥ!
ከረመ ገዢው መግለጫ ሲሰጥ
ይሄ ግልጽ ነው ካጀማመሩ፣
የህዝቡ ምርጫ ጠቧል ድንበሩ
እህ ዛዲያማ!
እህ ዛዲያማ! ምን ልንገራችሁ፣
የኛን ሃገርም ታውቁታላችሁ
የአፍሪካ ምርጫ ካውሮፓዎች ጋር፣
የአፍሪካ ምርጫ ካሜሪካ ጋር፣
ምኑም አይገጥምም በባህል በዘር
የማስመሰያው ያፍሪካ ምርጫ፣
እያጋደለ ህዝብ እያንጫጫ፣
እስካሁን ዘልቋል አጥቶ መቋጫ
እህ ዛዲያማ!
እህ ዛዲያማ! በአንድ ጎጆ
እህ ዛዲያማ! እህ ዛዲያማ!
አንድ ቁርንጮ ይነጠፍና
ምርጫ በይፋ ይታወጅና
እህ ዛዲያማ!
እህ ዛዲያማ! ምን ልንገራችሁ፣
የኛንም ጉዳይ ታውቁታላችሁ
ህዝብ ጨብጦ ሙሉ ነፃነት፣
የሀገር የመንግሥት ባለቤትነት
መያዝ ካልቻለ በነፃ ምርጫ፣
መቅመሱ አይቀርም የገዢ ጡጫ
እህ ዛዲያማ!
እህ ዛዲያማ! ምን ልንገራችሁ
የአፍሪካን ምርጫ ታውቁታላችሁ።
ሚያዝያ 13 ቀን 2000 ዓ.ም. - ስዊድን
April 21, 2008 - SWEDEN