ተፈሪ መንግሥቴ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ውጋትሽ ውጋት ሆኖ ይውጋቸው

ስቃይሽና ጣርሽ ላልገባቸው

እህቴ አንችማ አረፍሽው

በግፍ ተወልደሽ በግፍ ያደግሽው

ግፍን በልተሽ ግፍ ራሱን ለሆንሽው

በግፍ ኖረሽ በግፍ ላለፍሽው

 

 

በግፍ መሬት ተወልደሽ

በግፍ ካገር ተሰደሽ

የግፍ መሬት ላይ ለቀረሽው

አንቺማ እህቴ አረፍሽው

በገዛ አገርሽ ያልተከበርሽ

በሰው አገርም ያልቀናሽ

ባገርሽ ሰዎች ተሺጠሽ

ለባርነት የተዳረግሽ

ሳይመሽ ቀኑ ጨልሞብሽ

ጨለማውም ተደቅድቆ

የመኖር ተስፋሽ ተሟጦ አልቆ

 

በግፍ ርቀሽ ተለግተሽ

ግፍ ሳይራራ ተቀብሎሽ

አንዴም ፋታ ሳይሰጥሽ

እሱው ራሱ ሸኘሽ

ይብላኝ ለነሱ ለቀሪዎች

በሲቃሽ የቀለዱ ግፈኞች

የሊባኖስ ወንድ ጀግኖች

የቤይሩት ዘላን አረቦች

ከናት ያልተፈጠሩ ጨካኞች

ጉዳትሽን መግለጽ አቅቶሽ

መለመኛ አፍ ሳይኖርሽ

ቤይሩት ጯካ ለሆነብሽ ...

 

ይብላኝ ለኛ ለቀሪዎች

ባለሳምንቷን ጠባቂዎች

አንቺማ ተገላገልሽ

በምድር የራቀሽን

ሰላምሽን ኧገኘሽ

ባላውቅም የዎዲያኛውን

የዘላለም እረፍትን።


ተፈሪ መንግሥቴ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

 

March 15, 2012

Dallas

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ