ፋጣሪ ይጠብቀን!! (ቅዱስ ያሬድ)
ፋጣሪ ይጠብቀን!!
ቅዱስ ያሬድ
ስሜን መጠሪያዬን እራሴ ፈራሁት፣
መለስ ብዬ ሳየው ስራዬን ጠላሁት፣
እኔ ግራ ገባኝ እንዲ የቀለለው፣
ስሜ ሥስት ፊደል መለስ መባሉ ነው?
ምንድን ነው ሚስጥሩ ለአቤ የቀለለው።
ባልጠበኩት ሰዓት በተከበርኩበት፣
ውሸቴን ልጀምር በተቀመጥኩበት፣
ታላላቅ ሰው ሁሉ በሚያዳምጥበት፣
መለስ ብሎ ጠርቶ ከተተኝ ከሀፍረት፣
ለካ እንደዚህ ነው አምባገነን መሆን፣
ጉዳቱን ሳናውቀው ስልጣኑን እያየን፣
መከበርን ብቻ ሁሌ እንደተመኝን፣
መዋረድ እንዳለ፣
ሁሉንም እረስተን፣
አቤ የገላው ልጅ፣
ምርጥ የቁርጥ ቀን ልጅ፣
ይሄው በአሜሪካ ሁሉንም ነገረን፣
ከመንገርም አልፎ ብዙ ነገር አየን።
አኔ የምጸልየው ያውም በሰው ሀገር፣
አንገትን ከመድፋት እንዲህ ከማቀርቀር፣
ፋጣሪ ይጠብቀን በሰው ፊት ከማፈር።
ቅዱስ ያሬድ



