አበበ ሲያብብ (ወርቅእሸት ቸርነት)
አበበ ሲያብብ
ወርቅእሸት ቸርነት
እንደ አበበ አረጋይ አበባ ቢቂላ
የሚያብብ አበበ የት ተገኘ ሌላ?
አርበኛው አበበ ጣሊያንን የከላ
የቢቂላ አበበ ብዙ ወርቅ የበላ
የገላው አበበ በመለስ ላይ ሰላ
ወያኔ ሰመጠ በሻርክ ተበላ
በስብሰባ መሃለ የአበበ ቃል ጐላ
መንግስታት ሲመክሩ ምን እንደሚበላ
ገዳይ አምባገነን ራሱ ተበላ
ኢትዮጵያ እምትሻው ፍትህ ነው ነጻነት
ወያኔ ገለል በል ስለማታውቅበት
የፍትህ ጠበቆቸ ወርደዋል እስር ቤት
ሰው አስሮ አይወራም ስለ ምግብ እጦት
የጫካው አንደበት በአንድ ቃል ታሠረ
የአምባገነን ዱላ በ’ርሳስ ተሠበረ
ኢትዮጵያ ስታብብ አበበ ያብባል
ትውልድ ተከፍሎ ትውልድ ይከበራል
(ለነ አበበና ለፍትህ ጠበቆች)
ወርቅእሸት ቸርነት
May/ 2004



