አራት ሰው ባንድ አልጋ (ክንፈሚካኤል ገረሱ)

አራት ሰው ባንድ አልጋ
ክንፈሚካኤል ገረሱ
ቢተኙ አይደላቸው ቢነሱ እንቅልፋቸው፣
ቢለብሱ አይሞቃቸው በረዶ ገላቸው፣
ሁለቱም በየግል ጥንድ ሕልም አላቸው።
አንደኛው በመንፈስ በምናብ መንሳፈፍ፣
ሌላው በደመ-ነፍስ ግዑዝ መተቃቀፍ
እናም! እናማ!
ከቶ የት ይገኛል በዚህ መኻል ዋጋ፣
ባንድ ተሰድሮ አራት ሰው ባንድ አልጋ፣
አደጋ።
ክንፈሚካኤል ገረሱ
ኅዳር ፲፱ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.