20210302 adwa

Code of Conduct

ይናገራል ምግባር

ክንፈሚካኤል ገረሱ

ዓላማና ግብን አሳልጦ አስማምቶ፣

በሥራ በምግባር ስብዕናን ገንብቶ።

በታሪክ ማሕደር ውጤት አስከትቦ፣

ዝናን ተጎናጽፎ ለምልሞና አብቦ።

ትውልድን አንፆ በመልካም ክንውን፣

ተግባር እማኝ ሆኖ ተላብሶ አንቱታን።

ድንገት በዚህ መኻል፤

እህል ውኃ አክትሞ ዕድሜ ተገባዶ፣

ለዘላለም ቢያርፉ ሕላዌ ተንዶ።

በድን ጉድጓድ ቢወርድ ነፍስም ብትመጠቅ፣

አዛኙ ቢበዛ እሪታው ቢጸና ከበሮ ቢደለቅ።

ይሄ ሞት አይደለም የሥጋ መበስበስ፣

ከቶ አይጋርደውም ያካል መቆራረስ።

ድንጋዩን ፈንቅሎ ዘመናት ተሻግሮ፣

ይናገራል ምግባር አግዝፎና አክብሮ።


ክንፈሚካኤል ገረሱ

ታህሳስ ፩ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!