ዲያስፖራ አባ ወሬ

አባ ቤክሲሳ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

ክትባቴን ተከትበህ

ህዋሳትህ እንዳይሠራ፣

በቅኝቴ ስትዘምር

በልክፍቴ ስታጉዋራ

ካልደፈርከኝ በአንድነት

ዘረኛነቴን እያወገዝክ

በጎጠኝነት ካመለክ

 

ሕመሜን በሽታዬን

ቁስሌን ካልነካህማ

በቡድን ተከፋፍለህ

በጎሣ ከጠበብክማ፣

እልሃለሁ ምን ታመጣ

የቁም በድን አፈ ጮሌ

ተግባረቢስ ባልንጣ፣

የሰው ውራጅ ውሾ! ውሾ!

በራስ ሀገር

ችሎ! ችሎ! ችሎ ማደር።

 

እንደወገን!

ከተገበርክ አንድነትን

ተክህኖህ ወኔ ለብሶ

ተግባር ሰንቀህ ለወገንህ

የሀገር ጉዳት ካንተ ብሶ፣

ግንባር ለግንባር ስትጋፈጥ

በኢትዮጵያዊ ቆራጥነት

ውስጤን ሰንጥቀህ ገብተህ

ገመናዬን ስትገላልጥ፣

ወይኔ ያኔ የውርደቴ

የወያኔ ምፅዓተ ሞቴ።

 

አለዚያማ ምን ገዶኝ!

ስታር ባክስ ተኮልኩለህ

አውጫጭኝ በመቀመጥህ፣

ምን ተግዴ ለሰልፉማ

ተንሸራሸር ተንጎማለል

ተሞላቀቅ በከተማ።

 

ጧፍ መታደግ ተስኖህ

ስለፅልመት መተረክህ፣

እኔንስ ምን ሊጎዳኝ

አንተንስ የት ሊያደርስህ።

 

ይልቅ እንደልምድህ!

ለጥይቴ ግንባር ስጠኝ

እግሮችህን ለእግረሙቄ

እጆችህን ለካቴና

ንዋይህን ለስንቄ፣

መንበርህን ለሹሞቼ

ስብዕናህን ተመፅውቼ፣

እኖር ዘንድ ለዛሬ

ተባበረኝ እንደሥልጡን!

ዲያስፖራ አባ ወሬ።


 

አባ ቤክሲሳ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!