የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፪

ሁሉንም እኪሱ ከተታቸው ብሎ አንድ ሰው ነገረኝ
ገብቶ ነው መሰለኝ
አክቲቪስቱን ኪሱ፣
ጋዜጠኛን ኪሱ፣
ተቃዋሚን ኪሱ
ገጣሚውን ኪሱ፣
ከተታቸው ብሎ አንድ ሰው ነገረኝ
እሱንም አጣሁት ገብቶ ነው መሰለኝ።
ወለላዬ ከስዊድን (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)