የረቡዕ ግጥም ፫ኛ ዓመት፣ ቁ. ፲፪
ለምንም አትጠቅም
ከግለሰብ ሙግት፣ በግል አተካራ
ተደፍቀህ ከገባህ እንኳንስ ልትመራ
ከሜዳው ጠርዝ ላይ ይፈሳል ያንተ አቅም
ከቦታው ዞር በል ለምንም አትጠቅም
ሙሉውን አስነብበኝ ...ለምንም አትጠቅም
ከግለሰብ ሙግት፣ በግል አተካራ
ተደፍቀህ ከገባህ እንኳንስ ልትመራ
ከሜዳው ጠርዝ ላይ ይፈሳል ያንተ አቅም
ከቦታው ዞር በል ለምንም አትጠቅም
ሙሉውን አስነብበኝ ...”... በሬ አትሁን” ባለው
ያ መኪና ነጂ ሞተር አንቀሳቃሽ
አንድ ጥቅስ አለችው የጻፋት በብላሽ
”በፍየል ዘመን ላይ በግ አትሁን!” ያለው
ይኼን አባባሉን ምነው በለወጥው
”በአህያ ዘመን ላይ በሬ አትሁን!” ባለው!
ሙሉውን አስነብበኝ ...ዕድሜ
ይቺን ትንሽ ዕድሜ ይዘን የምንዞራት
እንኳንስ ንትርክ ፀብ ጨምረንባት
እፍ ቢሏት ጭልጥ ትንሽ ናት ደቃቃ
ፍቅር ለማጣጣም እንኳን የማትበቃ
ሙሉውን አስነብበኝ ...አብርሃም በየነ
ዐባይ ቢሻው ይጉረፍ በጣና ላይ ነግሶ
አሎሃ ይደፍርስ ተከዜም ደም ለብሶ
ማሂንም አቋሽም ጓንግም ቁልቁል ይፍሰስ ይትመም እያጓራ
መሻገሪያ ይንሳ እስኪያልፍ ክረምቱ በጉልበቱ ይኩራ
ምኑንም ምኑንም እርጥቡን ከደረቅ ያጉዘው ሙላቱ
እንደ አባት አደሩ እንደ ይትባህሉ ዛሬም እንደ ጥንቱ
የጎቤ መልኬም ሞት ደም በደም ይፀዳል ደም ነው ሥርየቱ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ወለላዬ ከስዊድን
አድዋ! በድልሽ የተገኘ ምሥራች
ጊዜው ረዘመ ብሎ ሳይሰለች
ዕድሜው በዕድሜ ላይ እየጨመረ
ጀግኖችን እንደገና እያነሳ እየደመረ
ዛሬም በልጅ ልጅ ልጅ ... ታሪክሽ ታወቀ
የድል ብሥራትሽ በዓለም ዓለም ዓለም ... አንጸባረቀ
የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ሻማ
መሆንሽ ተወራ አገር ለአገር ተሰማ
ሙሉውን አስነብበኝ ...