የረቡዕ ግጥም ፪ኛ ዓመት፣ ፴፪
ይገጥመዋል ፍዳ
ክብሩን የጠበቀ - የሚያስብ ለራሱ
ብዙ አይለፈልፍም - ቁጥብ ነው ምላሱ
ይህን ያላወቀ - ጠልቆ ያልተረዳ
ያልነካውን ነክቶ - ይገጥመዋል ፍዳ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ይገጥመዋል ፍዳ
ክብሩን የጠበቀ - የሚያስብ ለራሱ
ብዙ አይለፈልፍም - ቁጥብ ነው ምላሱ
ይህን ያላወቀ - ጠልቆ ያልተረዳ
ያልነካውን ነክቶ - ይገጥመዋል ፍዳ
ሙሉውን አስነብበኝ ...አብርሃም በየነ
ጨለማ ፅልመቱ ብርሃን አጥቶ
ሠላም እርጋታዋ በጦርነት ሙቶ
የዳኝነት ፍርዱ ፍትሁ ተዛብቶ
እውነትን ሞግቶ ሐሰት ረትቶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...አብርሃም በየነ
ዓለም ከርታታ ነች እንደየ ዘመኗ
ጊዜን ወዳጅ አርጋ አቁማ ከጎኗ
ግን ያነገሰችው ውሎ አድሮ ሲነጋ
ክብር የነበረው ድንገት ያጣል ዋጋ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ
ሀገር ማለት ልጄ፣ ሀገር ማለት፣
እንዳይመስልሽ የተወለድሽበት ቦታ፣ የተወለድሽበት አፈር፤
እትብትሽ የተቀበረበት፣ ቀድመሽ የተነፈሽው አየር፤
ብቻ እንዳይመስልሽ።
ሀገር ረቂቅ ነው ቃሉ፤
ሀገር ውስብስብ ነው ውሉ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሚስጥር ያስተርፋል
ብልህ አያወራም - ሁሉንም ዘርግፎ
ለራሱ ያስቀራል - ሚስጥር አስተርፎ
ሰነፍ ይሄን ጊዜ - ብዙ ይሳሳታል
አልታወቀም ብሎ - ጥፋት ያካብታል
ሙሉውን አስነብበኝ ...