የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፫

አንዱ እኔን ይመስላል
በጨመረ ቁጥር
እያንዳንዱ ቀናት
እያንዳንዱ ወራት
እያንዳንዱ ዓመታት
ከወየበው ቅጠል
ከሚረግፈው መሐል
ልቤ ድንግጥ አለ
አንዱ እኔን ይመስላል
ሙሉውን አስነብበኝ ...በጨመረ ቁጥር
እያንዳንዱ ቀናት
እያንዳንዱ ወራት
እያንዳንዱ ዓመታት
ከወየበው ቅጠል
ከሚረግፈው መሐል
ልቤ ድንግጥ አለ
አንዱ እኔን ይመስላል
ሙሉውን አስነብበኝ ...አክቲቪስቱን ኪሱ፣
ጋዜጠኛን ኪሱ፣
ተቃዋሚን ኪሱ
ገጣሚውን ኪሱ፣
ከተታቸው ብሎ አንድ ሰው ነገረኝ
እሱንም አጣሁት ገብቶ ነው መሰለኝ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ለዝች ትንሽ ዕድሜ
ቤት አልሠራም ያለው
መሃላ ደርዳሪው
በአብርሃም የቀናው
በቤት ኑዛዜ ውርስ
ተጣልተው እርስ በእርስ
ሳይሠራ ባገኘው
ወንድሙን ገደለው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...በዓለም ገበታ ከሚቀርበው ድግስ
ማንም ሰው አይችልም አንዷንም መጨረስ
ስለዚህ ሁሉንም ልትበላ አትንሰፍሰፍ
ድርሻህ ኢምንት ናት እሷን ቀምሰህ እለፍ!
ሙሉውን አስነብበኝ ...በየአውራ ጎዳናው ሲታዩ ሲሮጡ
ይመስል ነበረ ውጤት የሚያመጡ
ስንሔድ አንቸኩል እኛ ግን ቀስ ብለን
ሩጫ ሲጀመር እንቀድማቸዋለን
ሙሉውን አስነብበኝ ...