የረቡዕ ግጥም ፬ኛ ዓመት፣ ቁ. ፰

ሰው መኾን አትጥላ
ሰው ኾነህ ተፈጥረህ ሰው መኾን አትጥላ
እሚያዋጣህ የለም ሰው ከመኾን ሌላ
መነሻ ጥፋቱ ለሰው ሰው ችግሩ
ሰው ሳይኾን ሰው ኾኖ ከሰው ጋር መኖሩ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ሰው ኾነህ ተፈጥረህ ሰው መኾን አትጥላ
እሚያዋጣህ የለም ሰው ከመኾን ሌላ
መነሻ ጥፋቱ ለሰው ሰው ችግሩ
ሰው ሳይኾን ሰው ኾኖ ከሰው ጋር መኖሩ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ወሬን ንፋስ ይዞት፣ እያገላበጠ አገርን ሲያዞረው፣ ከመንገድ አግኝቶህ
ጓዙን አከፋፋይ፣ ትጉህ ሠራተኛ፣ አጋሰስ ፈረሱ፣ አድርጎ ከጫነህ
ከዛ ከውትብትብ ከማይታይ ገመድ፣ ማሰሪያ ሸምቀቆ አንተን ለማላቀቅ
ማንም ኃይል የለውም፣ ጸሎት አያድንህ፣ ፀበልም አይሠራ፤ ካንሰር ነው ተጠንቀቅ!
ሙሉውን አስነብበኝ ...ከሳሽ ነው በብርቱ፣ ከሳሽ ነው ዲያቢሎስ፣
ሁሉንም ይከሳል
አጣልቶ በጥብጦ፣ አጋጭቶ፣ ከፋፍሎ፣
ሕዝብን ያጫርሳል
ሰው እንደበደለን፣ ሰው እንደከሰሰን፣
ሰው እንደገደለን
አርገን አንገምተው፣ እላያችን ሰፍሮ፣ ውሎ ያደረብን
ክፉ ጠላት አለን!።
ሙሉውን አስነብበኝ ...አገሬ ብትለብስም ደርባ ደራርባ
ለብዙ ዘመናት የታሪክን ካባ
እላይዋ ነተበ አስቀየመ አርጅቶ
ሠርተን ሳናድሰው ከኛ ፍቅር ጠፍቶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...ቀኑን ተመልክተህ እወድቃለሁ አትበል
እውነተኛ ኾኖ አይረጋም ያንተ ቃል
እሱ በፈለገው ባሻው ቦታ ወርዶ
ሚጥለውን ያውቃል የዕለቱ በረዶ
ሙሉውን አስነብበኝ ...