የረቡዕ ግጥም ፫ኛ ዓመት፣ ቁ. ፳፱
አብሮ ከመቀበር
ስሩ መበስበሱን ንገሩት በይፋ
አጓጉል በመውደቅ ሰው እንዲያጠፋ
ለዚህ ነው የሚበጅ የቅርብ ሰው ምክር
እራሱም እንዲድን አብሮ ከመቀበር
ሙሉውን አስነብበኝ ...
አብሮ ከመቀበር
ስሩ መበስበሱን ንገሩት በይፋ
አጓጉል በመውደቅ ሰው እንዲያጠፋ
ለዚህ ነው የሚበጅ የቅርብ ሰው ምክር
እራሱም እንዲድን አብሮ ከመቀበር
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ጥበብ ተፀንሶ የተወለደባት፣
መላ-ምት በተግባር የተፈተነባት።
የሆነች መሠረት ለኢንጅነር ዶክተሩ፣
የቴክኖሎጂ አስኳል የዕውቀት መንበሩ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ላ'ምሮዬ ሰላም ስፈልግ አማራጭ፣
ነገሩ ሳይገባኝ ተጉዤ ባቋራጭ።
እርም ብዬ ትልቅ ውጥን ግዙፍ ሃሳብ፣
ትንሽ ሳልም ትርኪምርኪ ስሰበስብ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
የዘመኑን ፈሊጥ የመኖርን ምስጢር
ሳስተውለው ውዬ ቆሜ ስመረምር
ጥበቡ ገብቷቸው መሄጃውን አውቀው
መላ የጨበጡት ስሌት አስተካክለው
ከተጠቀሙበት ኃያል ብልሃቶች
አንዱ ማስመሰል ነው ለመኖር ከሰዎች
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ሌላን ሊያሽቆጠቁጥ
ስሙ ያልተጠራ ሥልጣን ያልጨበጠ
አለ በየቦታው ደረቱ ያበጠ
ምንም ተራ ቢሆን የግፈኛን ፈሊጥ
ይመኛል በልቡ ሌላን ሊያሽቆጠቁጥ
ሙሉውን አስነብበኝ ...