... ከዚኽ ወዴት? (ክፍል ስምንት - አያልሰው ደሴ)
የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል ስምንት
አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)
በውሳኔው መሠረት ጉባዔ አዘጋጁ ክፍል ስለዚህ ሀገር አቀፍ ጉባዔ ዓላማና አስፈላጊነት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለኢትዮጵያውያንና ለዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ በጥናት ላይ የተመሠረቱ ቅስቀሳዎችና ገለፃዎችን አድርጓል።
በጉባዔው አዘጋጅ አካል አባላት መኻል ልዩነቶችን ለመፍጠርና ለመከፋፈል እንዲሁም ከየአቅጣጫው እያንዳንዱ ዕቅድ እንዲሰናከል የተደረጉ እኩይ ጥረቶችን በአግባቡ በመቋቋምና በሽግግር መንግሥቱ ባለሥልጣናት የተደቀኑ መሰናክሎችን በመወጣት፣ ከሀገር ውጭም ይሁን በሀገር ውስጥ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የሲቪክና የሙያ ስብስቦች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ተሳታፊ የሆኑበት ሁሉን አቀፍ ሀገራዊ የሠላምና የእርቅ ጉባዔ ከታህሳስ ፱ እስከ ፲፫ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ እንዲካሄድ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቅና ተግባራዊ ማድረግ ቻለ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)



