አለቃ ተክሌ - ከቫንኩቨር-ኦታዋ (ካናዳ)

የ”ሞራል” ብቃትና የሞራል እጥረት ለነገሩ የተፈታው ማነው?

እንዳጋጣሚ ሆኖ ብርቱካንን ለመገምገምና በብርቱካን ላይ የ”ሞራል” ብያኔ ለመስጠት የሚያስችል የ”ሞራል” ብቃት የለኝም። ግን እንደ ባህል ይሄ “አንተ ወይም አንቺ ይሄንን ለማለት ወይም እንዲህ ለመናገር የሞራል ብቃት የለህም/ የለሽም” የሚል መፈክር ደሜን ያፈላዋል። ፖለቲከኞች ላይ የሞራል ፍርድ ለመስጠት የሞራል ብቃት አያስፈልግም። ፖለቲከኞችና ስራቸው እንደ መርህ ለማናቸውም ግምገማና ፍርድ የተጋለጡ ናቸው። ኦባማንና አስተዳደሩን ለመገምገም የአሜሪካ ህዝብ የተለየ የሞራል ብቃት አያስፈልገውም። መንጌ ሃራሬ ቤቱ ቁጭ ብሎ እሱ የሰራውን ቢሆንም እንኩዋን የሚደግመው መለስን መገምገምና ማብጠልጠል ይችላል። ብርቱካንንና ፖለቲካዊ እርምጃዋን ለመገምገም የግድ ለቅጽበትም ቢሆን በቃሊቲ መታሸት የለብንም። በቂ ምክንያት እስካለና በቅን ልቡና እስከተነሳሳን ድረስ የፖለቲካ መሪዎችን መገምገም መብት ነው። እነሆ ከብርቱካን ጉዳይ ጋር በተያያዘ መብቴን ልጠቀም ነው። እንዳጋጣሚ ሆኖ ግን በበጎ ነው።

 

ባለፈው እሁድ የተቀዳ የአዲስ ድምጽ ሬዲዮ ዝግጅት ላይ አንድ አድማጭ ስለብርቱካን መፈታት በሰጡት አስተያየት “የተፈታችው ብርቱካን አይደለችም? የተፈታው መለስ ነው”። እውነት ነው። እንዳትፈታ ባልጸልይም አንዳንዶች “ይድፋህ” እያሉኝም ቢሆን ለትግላችን የሚጠቅመው ብርቱካን ባትፈታ እንደነበር በጻፍኩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ብርቱካን ተፈታች። ማለቴ መለስ ተገላገለ። በኛ በተቃዋሚዎች እየተሳለቀም ቢሆን በብርቱካን መፈታት ሕወሀት/ኢህአዴግ እፎይ እንዳለ ለኢህአዴግ ቅርብ የሆነው ኢትዮጵያን ሪፖርተር ጽፏል። በዚህች ምስኪን ሴት እንግልት ማብቃትና በኚያ አረጋዊ እናቷ መከራ ማጠር እንዲሁም በከፊልም ቢሆን ድል ስላደረግን ተደሰትኩ። ግን ደግሞ በብርቱካን መፈታት በደስታ ዘልዬ ብቻ ማቆም አልፈቀድኩም። ይሄ ጽሁፍ ስለብርቱካን መፈታትና በፖለቲካችን ላይ ስለሚያሳድረው አሉታዊ ተጽእኖ የሚያትት ነው። ይሄ የማይመቸው ብዙ ድረ ገጽ ሳያጣብብ ጊዜውን ሳይገድል እኔንም ብዙ ርግማን ሳያሸክመኝ ለኔም ለሱም ደህንነት ሲል ከዚህ የክርክር ሰረገላ እዚሁ ይውረድ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ