የኢትዮጵያ ህዝብ፣ አገር-ወዳድና ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች እና ኢህአዴግ፤ ከዚኽ ወዴት? ክፍል ዘጠኝ

አያልሰው ደሴ (የግል አስተያየት)

በዶ/ር በየነ ጴጥሮስ (የሐድያ ብሔር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት) ሰብሳቢነት፣ በአቶ ከበደ ገብራይ (ኢዴኃቅ) ምክትል ሰብሳቢነት እና በዶ/ር ታዬ ወ/ሰማያት (የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር) ፀሐፊነት የተመራውና ከታኅሳስ ፱ እስከ ፲፫ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. በተካሄደው የአዲስ አበባው ”ሠላምና እርቅ በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ጉባዔ” ውሳኔ መሠረት በጉባዔው ላይ ከተሳተፉት ውስጥ ሰላሣ አንድ የፖለቲካ ድርጅቶችና የሙያ ማኅበራት በተገኙበት ታኅሳስ ፳፩ ቀን ፲፱፻፹፮ ዓ.ም.የኢሰዴአኃ ምክር ቤትን መመስረታቸው ይታወቃል።

 

ቆየት ብሎም ሰባት በሀገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች በአባልነት ምክር ቤቱን ተቀላቅለዋል። ኢሰዴአኅ በንድፈ-ሃሳብ ደረጃ በሁለት ሣምንት አንድ ጊዜ የሚሰበሰብ ከአባል ድርጅቶች አንድ - አንድ ተወካይ የሚሳተፉበት የምክር ቤት ጉባዔና በሣምንት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ በማድረግ የድርጅቱን የዕለት ተዕለት ተግባራት የሚሠራ፣ የሚቆጣጠርና የሚያስፈፅም ሰባት አባላት ያሉት ሥራ አስፈፃሚ አካል (ኮሚቴ)፣ እንዲሁም የፋይናንስ፣ የህዝብ ግንኙነት፣ የውጭ ግንኙነት እና የሕግና ደንብ አካላት (ኮሚቴዎች)፣ ከሀገር ውጭም ከዋናው ጽሕፈት ቤት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነትና ትስስር ያላቸው ቅርንጫፎች እንዲኖሩት ተደርጎ ነበር የተደራጀውና የተዋቀረው። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ