አብራሃም ለቤዛ

Ethiopian Navey
የኢትዮጵያ ባህር ኃይልና ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ

ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት በነበረችበት ጊዜ በቀይ ባህር ላይ ያላትን ቁጥጥር ዓለም አቀፍ ተቀባይነት የጎላ ነበር። በኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካል አቀማመጥ ምክንያት እና ምስጋና ለነገሥታቶቾ ታሪካዊ የባህር በር ባለቤትነትዋን አስከብረው ቢያልፉም፤ ይኽ ትውልድ ግን የተረከበውን አደራ መጠበቅ አልቻለም።

ዛሬ የአትዮጵያ ሕዝብ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሲሆን፣ ይህም በዓለም የባህር በር ከሌላቸው አገሮች አንደኛ እንድትኾን ያደርጋታል። በአፍሪካ ኢትጵያን ጨምሮ 15 አገሮች የባህር በር የሌላቸው ሲሆን፣ ነገር ግን 14ቱ የአፍሪካ አገሮች የሕዝብ ብዛታቸው ከ20 ሚሊዮን በታች ነው።

ይህን ማስታዎሻ እንድጽፍ ያስገደደኝ በቅርቡ ከአሰብ ወደብ ተነሳ በተባለ ንብረትነቱ በየመን ኾቲ ሚሊሻዎች ላይ ዘመቻ የከፈተው ጥምር ጦር የሆነ መርከብ በኾቲ ሚሊሻዎች አደጋ ተጣለበት የሚለው ዜና ነው።

የቀይ ባህር አካባቢ የቄሳርን ለቄሳር እንዲሉ ታሪካዊት እና ቀደመት የኾነችው ኢትዮጵያ በበላይነት መምራት ሲገባትና ለዓለም አገራት ምሳሌነትን ማሳየት ሲገባት፤ ዛሬ ከእጃችን አፈትልኮ የወጣበት ምክንት ታሪካዊ ውርደት መሆኑን መጠቆም እወዳለሁ።

ኤርትራ ሲያሻት ለኢራን (ሺአ ተከታይ)፤ ሲያሻት ለሳውዲ ዐረቢያ (ሱኒ ተከታይ) እያከራየች እርጥባን ብታገኝበትም፤ አካባቢውን የስጋት ቀጠና ኾኗል። የእኛ ደካማ መሪዎችም፣ ኤርትራ ብትፈልግ ግመሏን ውሃ ታጠጣበት ብለው ቢያጣጥሉትም ለኢትዮጵያዊያን ግን አጥጋቢ መልስ አይደልም።

Ethiopian Afar
“ግመሉ ሳትቀር የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ትለያለች” ሱልጣን አሊ ሚራህ

ግመሏ እያለችው ከቀየው ከቀይ ባህር አፋር (አፈር)፤

ላሟን ካልጫንኩ አለ ተሻግሮ በብድር።

ላሙ (ኬንያ)፤ በርበራ (ሶማሊያ)፤ ሱዳን ፖርት (ሱዳን) አሉን እያሉ ከማላዘን፤ ግመሏ ያለችበትን ቀይ ባህር ጠበቅ ማድረግ አማራጭ የለውም። ቀይ ባህር ተፈጥሯዊ የአፋር (አፈር) ሕዝብ ሀብት እንደሆነ፤ ይኸም በዓለም አቀፍ ሕግ ተቀባይነት እንዳለው (Law of intimacy) የምዳስስበት ፅሑፍ ይኖራል። ሱልጣን አሊ ሚራህ ስለአፋር ኢትዮጵያዊነት ሲያስረግጡ፤ “ግመሉ ሳትቀር የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ትለያለች” ነበር ያሉት። የአፍርን ሕዝብ ለሁለት የከፈሉት የእኛ መሪዎች (ጎረምሶች እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አገላለጽ) በሰንደቅ ዓላማችን እንደቀለዱ ወደ ግብዓተ መሬት ወረዱ። ስለ ቀይ ባህር የእኛነት ዳጉ ካደረግሁ በኋላ እመጣለሁ።

አንድ ቀን ግን ኢትዮጵያ ዳግማ በቀይ ባህር አካባቢ ታንሰራራለች። ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!