የፕ/ር አስራት ወልደየስ 18ኛ ሙት ዓመት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

Prof. Asrat Woldeyes
እውቁ የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ፕ/ር አስራት ወልደየስ

እውቁ የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ፕ/ር አስራት ወልደየስ የወያኔ አብዮት ማግስት በዜጎች ላይ የተፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት የህሊና እረፍት ነስቷቸው በሙያቸው ከበሽታ ሲፈውሱት የኖሩትን ኢትዮጵያዊ በፖለቲካ ትግል ከወያኔ የበቀል ደባ ለመታደግ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት ፕሬዝዳንት ሆነው ለወያኔ የውስጥ እግር እሳት በመሆናቸው በእስር ተሰቃይተው ከሞቱ (ከተገደሉ ማለት ሳይሻል አይቀርም) እነሆ ግንቦት 2009፣ 18 ዓመት ሆናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጥፋቱ የማን ነው? የትግሬዎች ወይንስ የአማሮች?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ጥፋቱ የማን ነው? የትግሬዎች ወይንስ የአማሮች?
እጅግ አሣፋሪና ታሪክ ይቅር የማይለው በደል “ወንድም በወንድሙ ላይ” ሲፈጽም በጣም አሳዛኝ ነው

‘ትግራይ ሪፐብሊክ’ ውስጥ ሰሞኑን የእግር ኳስ ጨዋታ በአማራና በትግሬ መካከል ተካሂዶ እንደነበርና ትግሬዎች አማሮችን ሰባብረው መጣላቸው ከተሰማ ሰነበተ፤ አጀንዳ መፍጠር የማይታክታቸው ትግሬ ወያኔዎች በዚህችም እያንጫጩን ነው። “እሰይ!” አይባል ነገር ሆኖብኝ እንጂ ትግሬዎቹ ያደረጉት ነገር የማይጠበቅ አልነበረምና ጥፋቱ ሙሉ በሙሉ የአማሮች እንደሆነ የማተቤን መመስከር እችላለሁ። የቀበጡ ለት ሞት አይገኝም፤ ፍየል ሲሰባ(ም) ሾተል ያሸታል። ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ። ደግሞ ተረት ለአማራ ሊያቅት?! በንግሊዝ አፍም ልጨምርልህ ከፈለግህ - “When its time has arrived, the prey comes to the hunter.”

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመለስን ልቃቂት አይቶ፣ ሰው እንዴት ያድራል ተኝቶ?!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

የመለስ ልቃቂት
"የመለስ ልቃቂት" የኤርምያስ ለገሰ መጽሐፍ

የፖለቲካ የበላይነትን በማረጋገጥ የሥልጣን ዕድሜን ለማራዘም ኢኮኖሚውን መቆጣጠር ወሳኝ መሆኑ ጥናትና ምርምር የሚጠይቅ የተለየ እውቀትም የሚሻ ጉዳይ አይደለም። ፖለቲከኞቹ ብቻ ሳይሆኑ ማንኛውም ሰው ሊያውቀው የሚችል ጉዳይ ነውና። አበውም "ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ" ይላሉ። ቁም ነገሩ ታዲያ ማወቁ ሳይሆን መተግበሩ ነው። እናም ወያኔ ይህን አውቆ ጠቀሜታና አስፈላጊነቱን ተረድቶ በኢኮኖሚ የበላይነት ፖለቲካውን ለመቆጣጠርና የሥልጣን ዕድሜውን ለማረዘም ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ባለሥልጣናት ለራሳቸው መጦሪያ ለልጆቻቸውም ተንደላቆ መኖሪያ የሚሆን ሀብት ማከበታቸውን የአቶ ኤርምያስ ለገሰ የመለስ ልቃቂት መጽሐፍ በመረጃና በማስረጃ አሳይቶናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአዲሱ ዘመነ መሳፍንት አክቲቪስቶች መነገር ያለበት ቁጥር 11

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

በልጅግ ዓሊ

Flag map of Ethiopia
ኢትዮጵያ

ኔ ምን አገባኝ - የምትሉት ሃረግ
እሱ ነው ያረዳት - አገሬን እንደ በግ
የምትለው ግጥም - ልጽፍ አሰብኩና
ምንአገባኝ ብዬ - ቁጭ አልኩ እንደገና
ኑረዲን ኢሳ

እነሆ እኛም “እነዚህ ሰዎች” እያልን፣ እየተማረርን አንዳንዴ ከሕዋ እንደ መጡ ሰዎች እየተመለከትናቸው፣ ሲደላን አብረናቸው ለመስራት ስንሞክር፣ ሲከፋን ትግሉን ጥለን እየሸሸን ስናማ፣ ስንቀማጠል በውጭ አገር በድረገጽ፣ በፌስቡክ፣ በቲዊተር ትግሉን እኛ ነን የምንመራው ስንል፣ ሲሰለቸን እጃችንን አጥፈን እየተቀመጥን፣ እነርሱን መታገል ሳንችል ስንቀር ከራሳችን እየታገልን ስንከፋፈል፣ ስንፈራ አጠገባችን ያለው ጠላት አድርግን ስንወጋ፣ አገራችንን ቀስ በቀስ ሲፈራርሷት አብረን እያፈረስን ሦስተኛው ዓሥርተ ዓመታት ዋዜማ ላይ ደርሰናል። ዛሬማ ብለን ብለን የወያኔን የዘር ፖለቲካ እኛው በመድገም አሳፋሪ ዜጋዎች ሆነን እንገኛለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወያኔ የዝርፊያ ድርጊት - በኤርምያስ ለገሰ የመለስ ልቃቂት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

አዩትና ልቡ እንደሞተበት

አባቱ ቀየ ላይ ወርደው ጠመዱበት

የመለስ ልቃቂት መጽሐፍ
"የመለስ ልቃቂት" የኤርምያስ ለገሰ መጽሐፍ

የኤርምያስ ለገሰን የመለስ ልቃቂት መጽሐፍ እያነበብኩ ነው። የወያኔ የዝርፊያ ድርጅቶችን አይነትና ብዘት በተለያየ ግዜ በተለያየ መንገድ እየተነገረም እየተጻፈም ያውቃናቸው ቢሆንም ይህን ያህል ዝርፊያ መፈጸማቸውን የሚያውቅ ብዙ ሰው የነበረ አይመስለኝም። ኤርምያስ የካድሬነት ቆይታውም ሆነ የኮሙኒኬሽን ምኒስቴር ዲኤታነቱ ዘራፊዎቹን ድርጅቶች በቅርብ ለማወቅ ያስቻለው በመሆኑ የሚያስነብበን በመረጃ እና ማስረጃ የተረጋገጠ እውነት ልብ ያቆስላል። ከወያኔዎቹ ድፍረት የእኛ ዝም ብሎ ሀገር ማዘረፍ ጥያቄ ያጭራል ቁጭት ይፈጥራል። ግና እኛ ከሕወሓት በተቃራኒ የቆምን ነን የምንል ወገኖች ከአንድ ሳምንት የሚያልፍ ቁጭት፣ ንዴት፣ ምሬት፣ ወዘተ አያውቀንም እንጂ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሞት ላይቀር፣ ተጠላልቶ መኖር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

የአቶ አሰፋን ነፍስ ይማር! በጥላቻ ለምንኖር የይቅርታ ልብ ይስጠን!

Assefa Chabo
አቶ አሰፋ ጫቦ

የት አባቱ ሞትም ይሙት!
እባካችሁ ዘመዶቼ ስሞት ሞትም አብሮኝ ይሙት
በሳቅ በደስታ ግደሉት
በሀሴት በእልልታ ውገሩት
ከአጥንት በታች ቅበሩት
እባካችሁ ለሞት የልብ ልብ አትስጡት
ናቁት አጥላሉት አውግዙት
በሙሾ ግነን አትበሉት
በሞቴ አታስደስቱት፣
(ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን)

የሰው መጨረሻው ሞት እንደመሆኑ ሞት በራሱ አያሳዝንም፣ አሟሟቱ እንጂ፤ ያለ ግዜው መቀጨት፣ በአሳቃቂ ሁኔታ መሞት፣ እውቀቱን፣ ልምዱን ችሎታውን ለአገር ጥቅም ሳያውል ወይንም ጀምሮ ሳይጨርስ መሞት ወዘተ ያሳዝናል። ያስቆጫል። ሟች በሕይወት በነበረበት ግዜ ለቤተሰቡ ምሰሶ ከሆነ ቤተሰቡ ለአንድ ሰሞንም ቢሆን ያዝናል። ለአገር ለወገን ጠቃሚ የነበረ ከሆነ ሕዝብ ያዝናል። በእኛ ባህል ደግሞ ሰው ሲሞት ክፉው ደግ፣ ጨካኙ ሩህሩህ፣ ንፉጉ ቸር፣ ፈሪው ጀግና ተደርጎ ይነገርለታል የሕይወት ታሪክ ተብሎ ይነበብለታል። ምን መጥፎ ቢሆን ሙት አይወቀስም። ሙት ወቃሽ አታርገኝ ይላሉ አበው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ