መፍትሔ የተራቡት የለውጡ ፈተናዎች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Dr. Abiy Ahmed

በቀለ ደገፋ፣ ኅዳር ፳፻፲፩ ዓ.ም.

በጠ/ሚ ዐቢይ የሚመራው የለውጥ ሥርዓት ወደሥልጣን ከመጣበት ዕለት አንስቶ እጅግ የሚያስደንቁና አንዳንዴም ለማመን የሚቸግሩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። በጥቂቱ ለማስታወስ - በወያኔ የማሰቃያ ቤቶች ተወርውረው የነበሩ ንጹሕንን ነፃ ማውጣት፣ በፖለቲካ አመለካከታቸው ሳቢያ ከአገር የተሰደዱ ኢትዮጵያውያንን ወደ ውድ አገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ፣ አሸባሪ ሲባሉ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅቶችን ወደ አገር ገብተው በነፃ እንዲንቀሳቀሱ ማድረግ፣ መቀመጫቸውን በውጭ ያደረጉ የመገናኛ ብዙኀን ሕዝብን በቀላሉ እንዲደርሱ እድል መስጠት፣ ትርጉም-አልባ የነበረውን የኢትዮ ኤርትራ ፀብ በእርቅ መፍታትና ብሎም በአፍሪካ ቀንድ የሰላም አየር እንዲነፍስ ማድረግ፣ ተለያይተው የነበሩ የቤተክርስቲያን አባቶችን በማስማማት የቅዱስ ሲኖዶሱን አንድነት መመለስ፤ እንዲሁም በባዕድ አገራት ለእስር ተዳርገው የነበሩ ኢትዮጵያውያንን አስፈትቶ ወደአገራቸው ማምጣት የሚሉት ይጠቀሳሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አርበኞች ግንቦት 7 እና ቀጣይ ተግባሩ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Dr. Berhanu Nega and Mr. Andargachew Tsege

ስሜነህ ታምራት (ከስዊድን)

ዛሬ ኢትዮጵያችን በሰላማዊ ሽግግርና "በየአብሮነት ልዩነት" መርኅ በዴሞክራሲያዊ ግንባታ ላይ ትገኛለች። ስለሆነም ከዚህ ቀደም ያልተጠቀምንባቸውን አጋጣሚዎች ሁሉ በትምህርትነት ወስደን፤ ዛሬ የተፈጠረው ሁኔታ እንደትናንቱ እንዳያመልጠን ብዙ እጅግ በጣም ብዙ የሆነ ትዕግሥትና ብሔራዊ ትኩረት የምናደርግበት የለውጥ ነጋሪት እየተጎሰመ ያለበት ጊዜ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጅምሩ ጥሩ ነው - ግን እነ በረከትና ካሣ ብቻ አይደሉም!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Bereket Simon

ነፃነት ዘለቀ

ብዙ ከዘገዬ በኋላም ቢሆን ብአዴን ነፍስ እያወቀ መምጣቱን በግልጥ እያየን ነው። ከዘላለም ባርነት የአንድ ቀን ነፃነት እንደሚሻልም እየተገነዘበ እንደሆነ በአንዳንድ ያልተለመዱ መልካም ተግባራቱ እየገለጸ ነው። ለምሣሌ በድኩማኖቹ ወያኔዎች የማንአለብኝነት ግልጽ ጣልቃ ገብነት ምክንያት በመካከሉ ተሰግስገው በነበሩ የሕወሓት ተወካዮች በነበረከት ስምዖንና ካሣ ታደሰ (ጥንቅሹ) የፊጥኝ ታስሮ ሲሰቃይ መኖሩን ተገንዝቦ እንደተባለው እስከፊታችን መስከረም 2011 ዓ.ም ድረስ እነሱን የማገድ እርምጃ መውሰዱ እየተዘገበ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአውራ ፓርቲው መሪነትና የ''አጋሮች'' እጣ ፈንታ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive
Bereket Simon

ዩሱፍ ያሲን - ከኦስሎ

በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እረፍት ማግስት የህልፈታቸው እንደምታዎችን አስመልክቶ ኢሳት ለአንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌና ለእኔ ቃለ መጠይቅ አድርጎ ነበር። የዛሬ 6 ዓመት መሆኑ ነው። በእሳቸው ሞት አባት አልባ (Orphan የእሳቸው ቃል ነው) እጓለ መውታ ይሆናሉ ያሏቸው ቅርበት የነበራቸው የሁለት ሰው ስም ጠቅሷል። ወይዘሮ አዜብ መስፍንንና አቶ በረከት ስምዖን። ትንበያው የያዘላቸው ይመስላል። ሁለቱን የፖለቲካ ስዎች የመለስ ዜናዊ ሞግዚትነት ማጣት የፖለቲካ ኮከባቸው እያዘቀዘቀ መጥቶ ኮስምነው፣ ኮስምነው ለጥቃት አመቻችቶ አጋለጣቸው። የፖለቲካ እጓለ ሙታን ቢባሉ አያስገርምም ለማለት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዐቢይ ዐቢይ ተግባር - ኢትዮጵያን ከማንነት ፖለቲካ ማፅዳት (De-ethnization)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive
Dr. Abiy Ahmed

ዩሱፍ ያሲን (ከኦስሎ፣ ኖርዌይ)

አሁንም ተስፋና ስጋት ጐን ለጐን እየተጓዙ ናቸው፣ በኢትዮጵያችን። እርግጥ ተስፋው እየፈካ፣ ስጋቱ እየደበዘዘ ይገኛል መባሉ ተገቢ ይመስለኛል። ምክንያቱ እውነታውን የሚያንጸባርቀው እሱ ነውና። ስጋቱ እየተነነ፣ ተስፋው ''ምኅዳሩን'' ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠረ ነው የሚል ተስፋ ያልሰነቀ ኢትዮጵያዊ ማግኘቱ እያስቸገረን ሆኗልና። የኻይር ወሬ በሽበሽ ነው፤ አልፎ አልፎ የግጭቶችና የመፈናቅሎሽ ዜና ቢያስበረግጉንም ቅሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እኛን በነሱ ውስጥ አየሁት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
PM. Dr. Abiy Ahmed addressing the parliament

ነፃነት ዘለቀ

“ከሰው መርጦ ለሹመት፣ ከእንጨት መርጦ ለታቦት” ይባላል። ይሁንና እንዳለመታደል ሆኖ በኔ ዕድሜ ይህ አባባል እውን ሲሆን ማየት አልቻልኩም። ከአሁን በኋላ ግን ተስፋ ያለኝ ይመስለኛል። ዕድሜ ለዕንባ አባሹ አንድዬ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!