20210302 adwa

ማስታዋሻ ቁጥር 10፡ ዐቢይ አሕመድ፣ የኢትዮጵያ “ሕይወት አድን” ጠቅላይ ሚኒስትር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
PM Abiy Ahmed with freed Ethiopian prisoners in Egypt

ፕሮፌሰር አለማየሁ (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

የጸሐፊው ማስታዋሻ፡ በዚህ ማስታዋሻ ውስጥ ሁለት ትችቶች አሉ።

የመጀመሪያው እና “አጭሩ“ (ቢያንስ እንዲህ እያልኩ የምጠራው አስተያየት ከዚህ በታች ) የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ሕወሓት) በአሁኑ ጊዜ በትግራይ ክልል ውስጥ በመስጠት ላይ ስላለው አመራር የቀረበ ትችት ነው። ሁለተኛው ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያውያንን ከበርካታ ሀገሮች ከእስራት እና ከእስር ቤቶች በማውጣት እያደረጉት ስላለው ህይወት አድን ልዩ ስራ አድናቆቴን የገለጽኩበት የተለመደው ማስታዋሻ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማስታዋሻ ቁጥር 9፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በኢትዮጵያ “የተቀደሱት ሰላም ፈጣሪዎች ናቸው”

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለአገሬ)

ቅዱሱ መጽሐፍ እንዲህ ይላል፣ “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው።” (ማቴ፣ ፭፣ ፱) ለሰው ልጆች የሰላም እና የዕርቅን መልክዕክት ለማድረስ ዓላማ አድርገው ለሚንቀሳቀሱ ሰዎች የተሰጠ መርሆ ነው። በግለሰቦች እና በአገሮች መካከል እውነተኛ ሰላም የሚገኘው በእርቀ ሰላም ሂደት የተሰበረውን ግንኙነት ቀድሞ ወደነበረበት መመለስ ሲቻል መሆኑን የሚያስተምረን መልዕክት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ ያሉ እውነታዎች

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive
የወያኔ ጎምቱ አመራሮች

ክንፉ አሰፋ

የሕወሓት መግለጫ በመስመሮች መካከል ሲነበብ በተቀማ ጩኸት ሊመስል ይችላል። ከመቀሌው ዱለታ በስተጀርባ የነበሩ እውነታዎችን ለመዳሰስ የፖለቲካ ሊቅ መሆንን አይጠይቅም። ሕወሓቶች አብረው ወስነው ያስተላለፉትን ጉዳይ እንደመጋዣ አኝከው ሲያበቁ፤ ከብዙ ገጽ የክስ ቻርጅ ጋር ብቅ ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩን ለማስጠቆር የሄዱበት ርቀት ግልጽና መሳጭ ነው። ሰማይ ወጥተው ቁልቁል ቢወርዱም ግን፤ ከቶውንም የሕዝብ ቀልብ ሊስቡ አይችሉም። እኛ ከሌለን አገር ትጠፋለች ይሉት የነበረው ቁንጽል እሳቤ፤ እነሆ ፉርሽ ሲሆንባቸው፤ አዲስ ካርታ መዘዙ። የአዲሱ ትውልድ መሪዎች፤ ሕዝብን በኃይል ሳይሆን በፍቅር መምራት እንደሚቻል ሲያሳዩዋቸው፣ ወደ ኦሪት ዞር ብለው ከዘፍጥረት መጀመራቸው ይሆን? በአዲሱ ዜማቸው፤ ኢትዮጵያን ትተው ስለ ትግራይ መጮህ የያዙ ይመስላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ያለውን የለገሰ ንፉግ አይባልም”

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
Ethiopian Airlines for sale

ዮፍታሔ

ትሕነግ (የትግራይ ሕዝብ ነጻአውጭ ግንባር / ሕወሓት/ወያኔ) እብሪተኛ፣ ስግብግብ፣ ሕዝብን የምትጠላና ችግር ለመፍታት እውቀት የሌላት ድርጅት በመሆኗ እንጂ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የኢኮኖሚ ችግር አስከፊነት ከፖለቲካው የማይተናነስ መሆኑን በመግለጽ መፍትሔውንም የጠቆሙ በርካቶች ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአገራችን ላይ የተቃጣውን ባህላዊ ዘረፋ እንታደግ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive
Ethiopian and turism

ሥናፍቅሽ ግርማ

አገራት ለኢኮኖሚ ድጋፋቸው ከሚጠቀሙበት ስልቶች አንዱና ዋንኛው ያላቸውን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብት መንከባከብ፣ መጠበቅና በተቻለ መጠንም ማሳደግ እንደሆነ ይታመናል። አገራችን ኢትዮጵያ ያሏትን በተጠቀሱት ዘርፍ የሚገኙትን ሀብቷን በአግባቡ ከተጠቀመች የኢኮኖሚ አቅሟን ለማሳደግና በዚህም የሕዝቧን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል እንደምትችል አያጠያይቅም። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተሰማራበት የሥራ ዘርፍ በመትጋት አገራዊና ወገናዊ ኃላፊነትን ለመወጣት የበቃን ሆነን መገኘት አለብን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ማስታዋሻ ቁጥር 8፡ የኢትዮጵያው ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ እባክዎትን፣ እባክዎትን በዩናይትድ ስቴትስ የእኛ እንግዳ ይሁኑ! (ግልጽ ደብዳቤ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active
PM. Dr. Abiy Ahmed

 ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

(የግልጽ ደብዳቤ ቅጅ)

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

C/o የኢትዮጵያ ኤምባሲ

3506 International Dr., NW
ዋሺንግተን ዲሲ. 2008

ውድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡

ሠላም ለእርስዎ ይሁን!

ቀደም ሲል ተይዞ በነበረው ፕሮግራም መሰረት በሀምሌ መጀመሪያ አካባቢ ዩናይትድ ስቴትስን እንደማይጎበኙ ተገንዝቢያለሁ።

የሚቻል ከሆነ በሀምሌ ውስጥ ተይዞ በነበረው የጉብኝት ፕሮግራም መምጣት በዩናይትድ ስቴትስ ካሉ በርካታ ደጋፊዎችዎ እና መልካም አሳቢዎችዎ ጋር በቀጥታ እንዲገናኙ እርስዎን በማክበር ለመጠየቅ እና ለመማጸን ነው ይህንን ደብዳቤ እየጻፍኩ ያለሁት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!