“የብሔርና የግለሰብ መብት ጥያቄ በኢትዮጵያ - ትናንትናና ዛሬ” በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ባለፈው ሣምንት ቅዳሜ ታህሳስ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. “መድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ” (የምክክር መድረክ) የተሰኘው ድርጅት በኢምፔሪያል ሆቴል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ስድስት ምሁራን የውይይት ጽሑፍ ማቅረባቸውን መዘገባችን አይዘነጋም። የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳም አንዱ ጽሑፍ አቅራቢ የነበሩ ሲሆን፣ “የብሔርና የግለሰብ መብት ጥያቄ በኢትዮጵያ - ትናንትናና ዛሬ” በሚል ርዕስ የመወያያ ጽሑፋቸውን አቅርበዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“የፖለቲካ ድርጅቶች የሕብረት ጥያቄ በኢትዮጵያ - ትናንትና እና ዛሬ” ከስዬ አብርሃ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 18 ቀን 2001 ዓ.ም. “መድረክ ለዲሞክራሲያዊ ምክክር በኢትዮጵያ” (የምክክር መድረክ) የተሰኘው ድርጅት በኢምፔሪያል ሆቴል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ስድስት ምሁራን የውይይት ጽሑፍ ማቅረባቸውን መዘገባችን አይዘነጋም። አቶ ስዬ አብርሃ “የፖለቲካ ድርጅቶች የሕብረት ጥያቄ በኢትዮጵያ - ትናንትና እና ዛሬ” በሚል ርዕስ ጽሑፍ አቅርበዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በእውኑ ብርቱካን ከቴዎድሮስ ታንሳለችን?! (አባኪያ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

እውነት እውነት እላችኋለሁ - አታንስም!!

አባኪያ  

ብርቱካን፤ እነሆ ሌላ ታሪካዊ ቅጽበት መጣ። ታስሮ የሟሟ የለም። ቴዲም አልሟሟ። ዶ/ር ታዬም። ታምራትም እንዲሁ። አሁን ያ ታዬ እዚያው እንደታሰረ ቢቀር ይሻለው ነበር እዚህ ከሚርመጠመጥ። ሆነ ሀኦነነ፤ ብርቱካን ሆይ፤ ብትታሰሪ በቅሌት አይደለም። ወይም በስርቆት። ለመብትሽና ለኢትዮጵያዊያን መብት ባደረግሽው በምታደርጊው ተጋድሎ እንጂ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቫንኩቨር እየተሰናዳች ነው፤ ጀግናዋን ልታስብ፣ ለእስረኛዋ ልትመሰክር፣ የተገፉትንም ልትዘከር!

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ቫንኩቨር እየተሰናዳች ነው፤ ጀግናዋን ልታስብ፣ ለእስረኛዋ ልትመሰክር፣ የተገፉትንም ልትዘከር

 

አሁን የምጣችን መሀል ላይ ነን። ይሄንን ለመረዳት ደግሞ “ጌታን መቀበል” የለብንም። ስለነጻነታችን፡ ሰዎች ይታሰራሉ። ስለ አንድነታችን ሰዎች ይገደላሉ። ስለ ፍትሀችንም ሰዎችም ይሰደዳሉ። አካላቸውም ተሰናክሎ ይቀራል። “እኛ ግን ምንም እንዳልተፈጠረ ሕይወታችንን እንቀጥላለን” ብለን ጽፈናል፤ ከዚህ በፊት። በርግጥ ክርስቶስ ስለሞተ፣ ነቢዩም ስላለፉ አለም መሽከርከሯን አላቆመችም። እኛ ቫንኩቨራዊያን ግን ይሄንን መለወጥ፣ ይሄንን መገልበጥ፣ ይሄንን መነቅነቅ ሻትን። ሰዎች በተገደሉ፣ ሰዎች በተሰደዱ፣ ሰዎች በታሰሩም ጊዜ ሕይወታችንን ብቻ ከማሳደድ አለማችንን ብቻ ከማሽከረከር ባሻገር፤ አለማችንን የምናቆምበት፤ በጭፈራችን ውስጥ፣ በልደታችን ውስጥ፣ በስብሰባችን ውስጥ፣ በደስታችንም ውስጥ ሁሉ፤ እነዚህን የተሰዉትን፣ የታሰሩትን፣ የተሰደዱትን፣ አካላቸውም የተሰናከለውን የምናስብበት ቅጽበት እንደሚያስፈልግ አምነን። እነሆ ቫንኩቨር እየተሰናዳች ነው። ሙሽሮቿን ልታስብ፣ ሙሽሮቿን ልትዘከር። ለታሰሩት አጋርነቷን ልትገልጽ። የኢትዮጵያን ግዛት ካካለለው ሰፊው እስር ቤት ወደ ጠባቡ ቃሊቲ ወይንም ዝዋይ ያለፍትህና በበቀል የተዘጋባቸውን ልታስብ እየተዘጋጀች ነው።

 አሁንስ የነኚህ ሰዎች ንቀት ጣሪያ ነካ። ቴዲ የመጀመሪያ አይደለም። ቴዲ የመጨረሻም አይደለም። ስንታሰር ኖረናል። ላልተወሰነ ጊዜም ስንታሰር እንኖራለን። ለዚህ ነው በምጣችን መሀል ላይ ነን ያልነው። እስራታችንን ለማሳነስ ከዚህ ከምእራቡ አለም የምንወረውረው ድንጋይ መለስ ዘንድ ባይደርስም እንኩዋን፤ የምንለግሰው ሞራል ግን ወዳጆቻችን ታጋዮቻችን ዘንድ ይደርሳልና፤ እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ የእስራታችንንም ቀንበር ለመስበር የሚታገሉትን ግን ከማሰብና ከማመስገን ከማበራታታም ወደኋላ አንልም። ታጋዮች ሲረሱ ያማቸዋል። ይጸጸታሉ። ቴዲ በዘፈኑ እንዲጸጸት አንፈልግም። ምነው ባልዘፈንኩ እንዲል አይሻም፡ ማህበረ-ቫንኩቨራዊያን። እንኩዋን ዘፈንኩ፤ እነሆ ትውልድ ሁሉ ያስታውሰኛል እንዲል እንጂ።

የቴዲ መታሰር ልክ እንደ ኦባማ መመረጥ “Symbolic” ነው። የኦባማ መመረጥ ግን ለብዙዎች የባርነት ቀንበር የመሰበሩን፣ የቀለም መጋረጃ መቀደዱን፣ የእኩልነት ዳር መጀመሩን፣ የዘር መድለዎ ማብቂያ መቃረቡን፣ ያ ማርቲን ሉተር ኪንግ ያለመው የተራራ ጫፍ መድረሳቸውን ምሳሌ ያበስራል። የቴዲ አፍሮ መታሰርም፤ በተቃራኒው ቢሆንም ምሳሌያዊ ነው። ይሄ የተበላሸ ስርአት የሰዎችን ሀሳብ ለማፈን የት ድረስ እንደሚወርድ የሚያሳይ ነው። የነዚህን ሰዎች ቂመኝነትና በመንግስታችን ከመጣ ዘፋኝም ይሁን ቄስ፤ ለማኝም ይሁን መምህር፤ ህጻንም ይሁን አዋቂ አንተውም አመለካከት ያሳያል። ጠብ-መንጅ አነስተው ተኮሱብን፣ ቦንብ አፈነዱብን፣ ዘር አጠፉ ወይም ለማጥፋት ሞከሩ አንድ ነገር ነው። ሰው ዘፈነ ተብሎ እንዴት ይታሰራል። እንዴት ያለ የዴሞክራሲ ጥግ ላይ ደረስን ጎበዝ? “ደጉ ይገልጣልን ድጋሜ ገደሉት” አለ በቴዲ አፍሮ መታሰር ያዘነው አበበ በለው። ስለዚህም ነው የቴዲ መታሰር የዚህ ስርአት ወጥ መርገጥ ሌላ ምሳሌ ነው ያልነው። የታሰሩትን ማሰብ ደግሞ በሰማይም በምድርም መልካም ነው። ሰምታችሁ ጠግባችሁት ይሆናልና። ያንን የመጽሀፍ ጥቅስ አላነሳላችሁም። “ስታሰር አልጠየቃችሁኝም፣ ስታመም አልጎበኛችሁኝም፣ ስራብ አላበላችሁኝም …” ይመጣል።

 

ቴዲ አይሟሟም። ባይታሰር መልካም ነበር። ቢታሰርም ግን ቀድሞውን እስር ቤት ነው። የቴዲ ጀግንነቱም ኢትዮጵያዊነትንና ፍትህን የሚሰብኩ ዘፈኖችን መዝፈኑ ብቻ አይደለም። እነዚህን ሰዎች የሚናደፍ ዘፈን ዘፍኖ እዚያው እኛ በሰበብ አስባቡ ጥለናት ከሸሸነው ኢትዮጵያ ሙጭጭ ማለቱ ነው። ሰው ገደልክ ብለው ቢከሱትም እንኩዋን፤ እዚህ እምእራብ፣ ከእኛ ምኩራብ ሊቀር አልፈለገም። “ቀድሞውንም ከሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ጋር ታስሯል” አለ አንዱ ወዳጃችን። ልዩነቱ የአሁኑ እስር ቤት ጠበበ። ቴዲና ሀሳቡ፣ ቴዲና የዘመረለት ፍቅር፤ የዘመረለት የእኩልነትና የፍቅር ራእይ ግን አይታሰሩም። ያሳወቀኝ ያ ህዝብ ነው። ያከበረኝም ያ ምስኪን የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው። ከኢትዮጵያ ብርቅ ቀኟ ይራቀኝ ብሎ እዚያው አገሩ ከተመ። እስሩን አጠበቁበት። የሱንም የሌሎችንም ሞራል ለመንካት። የገረመንስ የዚህ ልዑል የሚባል የገብረማሪያም ሳይሆን የገብረ ሰይጣን ልጅ ነው። ልጆች የሉትም? ሚስት የለችውም? እቁብና እድር፤ ማሀበር የለውም? ጽዋም አይጠጣም? ነው ወይስ እቁቡን ወደነአላሙዲ አዞረ? መቼም እዚህ ቁጭ ብለን እንደው በደፉት አንልም። ግን ይሄ “ዳኛ” ሳይሆን መጋኛ ነው። ሽብርተኛ። ሕወሀት-ሰራሽ ሽብርተኛ። ሽብርተኛ ደግሞ በተገኘበት ዋጋ ይሰጠዋል። ይሄን መጋኛ በጸበልም ይሁን በመስቀል ለሚያጋጭልን ኢትዮጵያ ዛሬም ባይሆን አንድ ቀን ሽልማት ትሰጣለች።

  

ይህ የእስራት ጥግ ነው። እስከዚያው ግን ቴዲንም ይሁን ሌሎች ንጹሀንን ያሰሩ፣ የገደሉ፣ ያሰቃዩ፣ ወይንም በዚህ የመግደልና የማሰቃየት ሂደት የተባበሩ በሙሉ ለፍርድ እስኪበቁ፤ እነሆ የሁለት ሺህ አስር የኦሊምፒክ አዘጋጅ፤ ታላቋ ቫንኩቨር እየተሰናዳች ነው። ቅዳሜ December 27th 2008 ቴዲንና መሰል የህሊና እስረኞችን ለማሰብ፤ ለህሊና እስረኛዋ፣ ለሙሽራዋ አጋርነትዋን ልትገልጽ ላይ ታች እያለች ነው። ሁላችሁም ተጋብዛችኃል። ያደረሳችሁ ሁሉ ኑ። ኑ እና በቴዲና መሰል ዘፈኖች እንጫወት። እንድትመጡም ብቻ አይደለም አሁን ባያደርሳችሁም በያላችሁበት ሰልፋችሁን፣ ዝክራችሁን፣ እንደቴዲ ዘፈን “ኡኡታችን” እስኪሰማ ኡኡታችንን እንድንቀጥልም ጭምር እንጂ። በድግሳችሁ ሁሉ ቴዎድሮስን አሰቡት። ይሄ ምክንያትም ነው። እንደ ኦባንግ፤ እንደ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ያሉ ድርጅቶችን ለመርዳት መልከም አጋጣሚም ነው። ያም ብቻ አይደለም። ሕዝባዊ ወያነ አርነት ትግራይ እንዲህ ያለውን ስራ እስከገፉበት፤ እኛም አንተኛም፤ ብንተኛም አናንቀላፋም፣ ብንጨፍርም ቴዲንና መሰል የህሊና እሰረኞችን አንረሳቸውም ለማለትም ጭምር ነው። ቫንኩቨራዊያን። በቴዲም ይሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እስራቱ በጠበቀ ቁጥር እኛም ቴዲንና መሰል እስረኞችን የጀግና ማእረግ እንሰጣቸዋለን። የአርበኝነት። የትግላችን ፊታውራሪነት። ቫንኩቨራዊያን።

 

አንድ ዕይታ አስራ አንድ አስተያየቶች፤ ስለቀጣይ “ምርጫ” እና ቀጣይ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች አካሄድ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

“ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መሳተፍ፤ መግባት አለባቸው” ተክለሚካኤል አበበ

በ2010ም እ.ኤ.አ. ይሁን ከዚህ በኋላ፡ መቼም “ምርጫ” ከተካሄደ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በኢህአዴግ መንግሥትነት በሚካሄድ ማናቸውም ምርጫ መሳተፍ ይገባቸዋልን? የሚለውን ጥያቄ፡ “አዎ መሳተፍ አለባቸው!” ብቻ ሳይሆን “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ መሳተፍ፤ መግባት አለባቸው” ማለቴ ብዙዎቻችሁን ሳያስገርም ምናልባትም ይሄ ሰው ምን ነካው? ጤነኛም አይደል እንዴ ሳያሰኛችሁ አይቀርም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሕገ መንግሥትና ሕገ አራዊት (ፕ/ር መስፍን)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ፕሮፌሠር መስፍን ወልደማርያም (ታኅሳስ 2001)

Prof. Mesfin Woldemariam“ሕገ አራዊት” የተፈጥሮ ሕግ ነው፤ በደመ-ነፍስ የሚንቀሳቀሱ ኹሉ ለመራባት የሚያስችላቸውን ግዴታቸውን የሚፈጽሙት በሕገ አራዊት ነው። የቀደመው አሁን ከአለው አይለይም፤ የወደፊቱ ከአሁኑ እንደማይሻል የታወቀ ነው። የቀድሞውም በጉልበት ነው፤ የአሁኑም በጉልበት ነው፤ የወደፊቱም በጉልበት ነው። የሕገ አራዊት መሠረቱ ጉልበት ብቻ ነው። ምግብ የሚገኘው በጉልበት ነው፤ ጉልበት ያለው ይበላል፤ ጉልበት የሌለው ለጉልበተኛው ምግብ ይሆናል፤ ጉልበት ያለው ይንደላቀቃል፤ ጉልበት የሌለው በየጉድጓዱ ይሽሎከለካል። ሙሉውን አስነብበኝ ...