ሽምግልና ወይስ የሕግ የበላይነት? (ነብዩ ግዛው)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ነብዩ ግዛው

በእንቢልታ ጋዜጣ ቅጽ 1 ቁጥር 49 እትም ”የፖለቲካ ውዝግቡና የሽማግሌዎች ሚና” በሚል ርዕስ የቀረበውን ዘገባ አንብቤዋለሁ። ጹሑፉ በጣም ጥሩና ሊነበብ የሚገባው ሲሆን፣ በውስጡ ቢካተት የበለጠ ጥሩ ይኾን ነበር ያልኩትን፤ ይችን ጽሑፌን ለአንባቢ እንድታደርሱልኝ እጠይቃለሁ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምርጫ ሌባ (ፕ/ር ዓለማየሁ ገ/ማርያም)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ሌባ! ሌባ! ያዘው የምርጫ ሌባ!

Prof. Alemayehu G.Mariamፕሮፌሠር ዓለማየሁ ገ/ማርያም

የታይላንድ ሕገ መንግሥታዊ ፍ/ቤት ባለፈው ሣምንት በምርጫ ያጭበረበሩ ሌቦችን ጉዳይ ተመልክቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሶምቻይ ዎንግስዋትና የስድስት ጥምር ፓርቲው አመራሮች በታኅሳስ 2007 ዓ.ም. በሀገሪቱ የተካሄደውን ምርጫ አጭበርብራችኋል በሚል ጥፋተኛ ብሏቸዋል። ግለሰቦቹ ጥፋተኛ የተባሉት የመራጮችን ድምፅ በመግዛት፣ ድምፅ በማጭበርበር፣ መራጮች የሚሰጡትን ድምፅ በማሳሳትና ሌሎች የምርጫ የማጭበርበር ተግባራት በመፈፀም ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ክፋትን የዘሩ መከራን ያጭዳሉ (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ዳኛቸው ቢያድግልኝ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

የፖለቲካ አመለካከትና አስተሳሰብ ሳይሆን ዛሬ ኢትዮጵያዊነት ወንጀል ነው። ፍቅር አያስከብርምና ይኸው ዛሬን ደግሞ ፍቅርን፣ መተሳሰብን፣ ይቅር መባባልን አሳስረን የእስር ቤታችንን አጥር እያጠባበቅን ነው። የፈራን ፈርተን ዳግም ቀና እንዳንል ስንረገጥ ታፋችንን በፈረቃ ለመስጠት ፈቃዳቸውን እየጠበቅን ’የባሰ አታምጣ!’ እንላለን። የመረጥነውን እምቢ ሲሉን ዝም ባልን፣ የመረጥናቸውም ግራ ሲጋቡብን ወደ ’አንድ ሁኑ!’ ማለት ባይቻለን ዛሬ ከቀሳውስቱ ልቆ ምህረትን የለመነ፣ ከጠቢባን ልቆ ፍቅርን የሰበከና በሚፈነጭበት ዕድሜው ብስለትን ያስመለከተ ወንድማችንን ለስድስት ዓመት ሊነጥቁን መወሰናቸውን ነገሩን። እግረ መንገዳቸውንም ’እስቲ የምትሆኑትን እናያለን’ ብለው እንደ ጠገበ ጅብ እያስካኩብን ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ ጥፋቱ ያስተሰርያል ማለቱ! (ኤፍሬም ማዴቦ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ኤፍሬም ማዴቦ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. )

በ1999 ዓ.ም. በተደረገው ህዝባዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ህዝብ ይበጁኛል ብሎ የመረጣቸውን የህዝብ ተወካዮች በግፍ አስሮ ለሁለት ዓመታት ካሰቃየ በኋላ በይቅርታ ተለቃችኋል ብሎ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያሾፈው የመለስ ዜናዊ መንግሥት ከሰሞኑ ውዱን የኢትዮጵያ ልጅ ቴዎድሮስ ካሳሁንን (ቴዲ አፍሮን) ካለ በቂ ምክንያት አስሮ፣ ካለ በቂ ማስረጃ ጥፋተኛ ነህ ብሎ ፈርዶበታል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ ክስ - እኛ ሁላችንም ነው የተፈረደብን

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ግርማ ካሣ (ከቺካጎ)

ሚያዚያ 8 ቀን 2000 ዓ.ም. ነበር ዝነኛው የኪነት ሰው ቴዎድሮስ ካሳሁን “ሰው ገጭተሃል” በሚል ክስ ነው ወህኒ የወረደው። እስር ቤት በገባ በስምንት ቀኑ “በርግጥ መንግሥት መረጃ ኖሮት ነውን? ወይስ ቴዲ የገዢው ፓርቲ ሰዎች ህዝብ እንዲሰማ የማይፈልጉትን መልዕክቶች በማቅረቡ? በርግጥ ሕግ የበላይ መሆን ስላለበት ነውን? ወይስ ሕግን እንደ ዱላ ተጠቅሞ የተቀየሙትንና የማይስማማቸውን ሰው ለማፈንና ለማስወገድ ስለተፈለገ ነውን? በኢትዮጵያ ፍትህ እንዲሰፍን፣ ሁሉም በሕግ ፊት እኩል ስለሆኑ ነውን? ወይስ በኢትዮጵያነት ላይ ያነጣጠረ ጥቃት?” የሚሉ ጥያቄዎችን በመጠየቅ መልሱን በቅርብ የምናየው እንደሆነ ገልጨ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሽምግልናውና ሽማግሌዎቹ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

 የቅንጅት አመራሮችን ከእስር በማስፈታት ኺደት የተሳተፈው የሽምግልና ቡድን፣ የኃይማኖት አባቶችንም እርስ በርሳቸውና ኦነግን ከመንግሥት ጋር ለማደራደር፤ ከኦነግ ጋር በተያያዘ በቁጥር ስር የዋሉ እስረኞችን ለማስፈታት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በሌላ በኩል ኦነግን ከመንግሥት ጋር ለማደራደር ሦስት አባላት ያሉት ሌላ ቡድንም ተቋቁሟል። እነዚህ የሽምግልና ቡድኖች በሀገራዊው ተጽዕኖ ላይ ምን ዓይነት የፖለቲካ ድባብ ያሳድራሉ? ስትል የሚመለከታቸውን የተለያዩ ሰዎች የጠየቀቸው የእንቢልታ ጋዜጣ ዘጋቢ ጽዮን ግርማ ስትሆን፤ ጋዜጣው ይህንኑ ዘገባ ለንባብ አብቅቷል። ሙሉውን አስነብበኝ ...