በዶክተር ፀጋየ አራርሣ “De-Amharicization” ቃል ላይ የሚሰማኝን ልበል?
ማስተዋል በለጠ
ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን መሃል የገባብን ወያኔያዊ ንፋስ ደግሞ ከሌላው ጊዜ ለየት ይላል። ከአንዱ ንትርክ ወጣን ስንል ሌላ ይተካል፤ “መቃቃርን አስወገድን፤ ወደ አንድነትም መጣን” ብለን ከመደሰታችን በአንዱ አቅጣጫ የካብነውን የሚያፈርስ ነገር ብቅ ይላል። ከለንደኑ የኦሮሞ የሕግ ምሁራን ስብሰባ ወዲህ እስከ አትላንታው የዚያው ስብሰባ ቀጣይ ክፍል ድረስ እየታዬና እየተሰማ ያለው ነገር ደግሞ ለብዙዎቻችን እምብዝም የሚጥም አልሆነም። ይሁንና ነገር ሁሉ ለበጎ ነው እንዲሉ ብዙ መረበሽ ያለብን አይመስለኝም። ሁሉም ነገር በጊዜው እየተፍረጠረጠ መውጣቱ ለቁስሎቻችን በአፋጣኝ መጥገግና ማንን ከማን ለይተን መጠጋት ወይ መራቅ እንዳለብን ለማወቅ ይጠቅመናል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...







