የአማራ ተጋድሎ ከዚህ ወዴት? (ክፍል ፪)
ሙሉቀን ተስፋው
1. ምን አጣን?
እስካሁን ባካሔድነው ትግል በጣም ብዙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን አጥተናል። የአማራ እናቶች ዳግም ምርር ብለው አዝነዋል፤ አልቅሰዋል። ሕጻናትና ወላድ እናቶች ሳይቀሩ አማራ በመሆናቸው ብቻ ተጨፍጭፈዋል። በሺሕ የሚቆጠሩ የአማራ ልጆች በየአካባቢው በሚገኙ እስር ቤቶችና የማሰቃያ ቤቶች ታጉረው የወያኔ ቶርቸር ሰለባ እየሆኑ ነው። መተማ ውስጥ በርካታ አማሮች በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። እንደበለጠ ንብረቱ ቸኮለ ያሉ ብሩህ አዕምሮ ያላቸውና የአማራ ሕዝብ ተስፋ የሆኑ ወንድሞቻችን በአነጣጥሮ ተኳሾች ተገድለዋል። አሁንም በአማራ ክልል በየቀኑ ልጆቻችን ይገደላሉ፤ ይታሰራሉ። ከዚህም አልፎ የአማራ ተጋድሎ ያርበተበተው ወያኔ፣ በአማራና በሌሎች ሕዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር ከአማራ ክልል ውጪ በሚኖሩ አማሮች ላይ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ከፍቶ እያሰቃያቸው ይገኛል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...







