ፉክክር፣ ብሔረተኛነትና ትብብር በለውጡ ዋዜማ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዩሱፍ ያሲን

Gonder protest

1. ኢትዮጵያ በለውጥ ዋዜማ

በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ቀጣይነት ሊኖረው የሚችል ሁኔታ አይደለም (Unsustainable) ሲባል ሰንበትበት ብሏል። አንድ ሐሙስ ቀረው እየተባለ መነገር የጀመረው ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ነው። የሥርዓቱ ዕድሜ ካንድ ሐሙስ ይልቅ ከላይ ወደ ዜሮ በሚደረግ የኋሊት መቁጠር የሚዳዳቸው ታዛቢዎቹም አሉ። በፈረንጅኛው Count Down የሚሉት ስሌት መሆኑ ነው። እንደ ተለመደው ኢትዮጵያ ታሪካዊ መጋጠሚያ ላይ ቆማለች፣ በመንታ መንገድ ላይ ናት መባሉ እንደገና እየተዘወተረ መጥቷል። ሁሉም ግን ኢትዮጵያ ወዴት? የሚለውን ጥያቄ እያስጨነቀው ነው። ኢትዮጵያ አሁንም ታሪካዊ መጋጠሚያ ላይ መቆሟ አያነጋግርም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማኅበራዊና የሕብረተሰብዓዊ ጥያቄ ወይም የብሔር/ብሔረሰብ ጥያቄ?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

”እባብ ወተት ጠጥታ መርዝ ትተፋለች፣ ቅዱስ ግን መርዝ ጠጥቶ ወተት ይተፋል!“ Azmuto

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

The question of nationality

መግቢያ

አሁን ያለንበት ዘመን 21ኛው ክፍለ-ዘመን ነው። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ፣ ብዙ የምዕራብ አውሮፓ ሀገሮችና አሜሪካንንም ጨምሮ፣ እንዲሁም ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ፣ ዛሬ ደግሞ ቻይና በሳይንስ አማካይነት የቴክኖሎጂ ምጥቀትን በማግኘት አነሰም በዛም የተረጋጋ ሕብረተሰብ ለመገንባት ችለዋል። በተለይም ባለፉት 40 ዓመታት የተፈጠሩትና ገበያ ላይ የዋሉት ቴክኖሎጂዎች ቀደም ብለው ከነበሩት ቴክኖሎጂዎች ጋር ሲወዳደሩ በጥራትም ሆነ በምቾት እጀግ ተሽለው የሚገኙ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቦይ ዘባረቁ? ሰምሃልስ?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

እንግዳ ታደሰ ከኖርዌይ

Aboyi Sibhat

ያንን ገለባ ልጅ ከደጅ የወደቀው
አድራሻህ ወዴት ነው ብለህ አትጠይቀው
የነገው ነፋስ ነው መንገዱን የሚያውቀው።
በዕውቀቱ ስዩም

ጥቅምት 5 ቀን 2009 ዓ.ም. የሸራተን አዲስ የላሊበላ አዳራሽ ቲያትር ቤት መጋረጃ ለተደራሾች ተገለጠ። ሁለት መቶ ሃምሳ ታዳሚዎችን ባጨናነቀ ሁኔታ የትያትር ቤቱ አዳራሽ ሞልቶ ነበር። ”በዲሞክራሲያዊ ግንባታ ችግሮች ላይ የተሰነዘሩ ምልከታዎች” በሚል መርሃ ቃል በአቶ በረከት ሰምዖን መርሃኤ ተውኔት አዘጋጅነት፣ በልደቱ ተዋኝነት የተካሄደ ስብሰባ። አዳራሹን ያለስሙ ቲያትር ቤት ያልኩት ጠፍቶኝ አይደለም። ከወሎዋ ላሊበላ ምድር፣ እስከ ሸራተኑ የላሊበላ አዳራሽ ድረስ እነኝህ ሁለት ሰዎች እንዴት እየተደጋገፉ እንደሚያቄሉን ስለገረመኝ ነው ቲያትር ቤት ያልኩት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለወያኔ ዕድሜ ማራዘሚያ በተዘጋጀ መድረክ ተቀዋሚዎች ምን ይሠራሉ?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

Lidetu Ayalew (M) and Bereket Simon (L)

የፖለቲካ ድርጅት የመገናኛ ብዙኃን ባለቤት እንዳይሆን የሚከለክለውን ሕግ በመተላለፍ ወያኔ ያቋቋመው ፋና ሰሞኑን አንድ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር። ውይይቱን በቀጥታ ስርጭት ሳይሆን ለእኛ ይገባቸዋል ብለው የመጠኑልንን አቀናብረው አስተላልፈውልን ተመልክተነዋል። ጽሁፍ አቅራቢዎቹ ተወክለው ይሁን ወክለው ባይታወቅም ከምሁራን ከባለሀብት ከተቀዋሚና ከኢህአዴግ ተብለው ነው የቀረቡት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሰመሃል መለስ የገባት መተካካት - ተቃዋሚዎች ያልገባቸው መታደስ!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ክንፉ አሰፋ

Semehal Meles

የአፈና ግዜ አዋጁን ተከትሎ፤ የህወሓቱ ፋና ብሮድካስቲንግ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያስተናገደው "የውይይት መድረክ" አዳዲስ ኩምክናዎችን ይዟል። ልደቱ አያሌውን በመሪ ተዋናይነት ያሳተፈውን ይህን አዲስ የበረከት ስምዖን ድራማ ብዙም ሰው አላየውም። ህዝቡ ፋና ሚባል ነገር እንደሬት መርሮታል። ገሚሶች ደግሞ በ"ቃና"ው "ጥቁር ፍቅር" ድራማ ተጠምደዋል። በዚህ ድራማ ልደቱ አያሌው መሪ ገጸ-ባህሪይ ተላብሶ ይተውን እንጂ፤ እንደወትሮው ቀልብ ሊስብ አልቻለም። በኢትዮጵያ ታሪክ ወያኔ መድብለ ፖርቲን የፈቀደ ድርጅት እንደሆነ በሙሉ አፉ ሲናገር እሱ አላፈረም። ከሱ ይልቅ የተሸማቀቁት እነ በረከት እና ስብሃት ናቸው። በልባቸው አበስኩ ገበርኩ እያሉ ... ጌታዎቹ ኀዘን ሲሰማቸው እሱ ያለቅሳል። በዚህ አቋሙ ከሦስተኛው መንገድ ወደ አንደኛው የተሸጋገረ ይመስላል ልደቱ። ለነገሩ እንጂ፤ ለሱ መገለባበጥ አዲስ ጉዳይ አይደለም!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሳይካተቱ የተረሱ አንቀጾች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አሰፋ ዳሞቴ (ከአዲስ አበባ)

The forgotten chapters in the state of Emergency

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ውስጥ ሆነን ሁለተኛ ሣምንታችንን ያዝን። ዕድሜ ለአዋጁ ገንዘቤም አፌም ዐረፉ። አሁን አፌን ሰብስቤ በጊዜ ወደቤቴ ከማምራቴ በፊት በየመሸታ ቤቱ እንደጣቃ ስቀደድ አመሽ ነበር። አንዱ ጆሮ ጠቢ ጠልፎ ቢወስደኝና ድራሼን ቢያጠፋው ለምግብ ያላነሱ ለሥራ ያልደረሱ ልጆቼ ወደ በረንዳ መበተናቸው አይቀርም። በሌላም በኩል አዋጁን ቀድሞ በተዘጋው ኢንተርኔት ሰበብ ብዙ ገንዘብ በቴሌ እበላ ነበር፤ አሁን ግልግል ነው። ሣር አልበላም እንጂ፤ በዚያም ላይ “እምቧ!” እያልኩ እንደከብቶቹ አልጮህም እንጂ፤ ዕድሜ ለህወሓት የለዬልኝ የቤትና የዱር እንስሳ ሆኛለሁ - በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንድ አይሉ ሁለት ዲፕሎማ ይዤ የማልናገር የማልጋገር የወያኔ ጥፍጥፍ ባሪያ ሆኜ መገኘቴ፤ የሰው ልጅ የደረሰበትን ኢትዮጵያዊ የዕድገት ደረጃ ያመለክታል። ግሩም ዕድገት! ግሩም እንከን የለሽ ዴሞክራሲያዊ ኢትዮጵያዊ ሩህሩህ መንግሥት!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ