የማንነት ፖለቲካ ጠንቆችና የአብሮነት አኗኗሪ መፍትሔ ፍለጋ
ዩሱፍ ያሲን (ደን ሐግ)
"It is NOT our differences that divide us. Rather it is our INABILITY to recognize, accept and celebrate those DIFFERENCES." Audre Lorde
ልዩነቶቻችን ውበታችን የሚሆኑት ስናስተናግዳቸው ብቻ ነው፤ አለበለዚያ ያወዛግቡናል። ዩሱፍ ያሲን (አርቲክል 2012)
1. የማንነት ጥያቄዎች በየፈርጁና በየመልኩ
እገሌ የሚባል ስብስብ ለመንግሥት ምክር ቤት የማንነት ጥያቄ አቀረበ። እገሌ የሚባለው ደግሞ በዚህ ክልል ሳይሆን በዚኛው ክልል ልካለል አለ። ሌላው እኛ መታወቂያ መለያ አጠራሬ ይህ ነው እንጂ ይህኛው አይደለም። አንደኛው ብሔረሰብ ልዩ ዞን (ኮንሶ) ሌለኛው ክልል (ሲዳማ) ይሰጠኝ የሚል ጥያቄ አቀረበ። ስብስቦች የማንነት ጥያቄያቸው በሕገ መንግሥት መሠረት ለመንግሥት ምክር ቤት አቀረቡ ሲባል እንሰማለን። ይህንን ጥያቄ ያቀረቡ የቅማነት፣ የቁጫ፣ የወልቃይት፣ የዱቤ ብሔረሰብ አባላት ተገደሉ፣ ታሠሩ፣ ተቀጡ፣ ወዘተ ሲባል እንሰማለን። ገሚሱ የማነት ጥያቄ ቀላል መልስ አለው። ገሚሱ ቀላል መልስ የለውም።
ሙሉውን አስነብበኝ ...







