በእርስ በርስ ጦርነት ድል ሃያ አምስት ዓመት ፉከራ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ይገረም አለሙ

Ginbot 20, 25th anv. ግንቦት 20፣ 25ኛ ዓመት

በእርስ በርስ ጦርነት ከሁለቱም ወገን የሚሞተው የአንድ ሀገር ልጅ ነው። አባትና ልጅ፤ ወንድምና ወንድም ከዛና ከዚህ ተሰልፈው የሚገዳደሉበት አጋጣሚም ይኖራል። ይህም በ17 ዓመቱ የርስ በርስ ጦርነት በግልጽ ታይቷል። ወያኔዎች ለድል የበቁት የኢትዮጵያን ሠራዊት ብቻ ሳይሆን ደርግን ተቃውመው ብረት ያነሱ፤ ነገር ግን ከዋሉ ካደሩ ለህወሓት ህልውና አስጊ ይሆናሉ ያሉዋቸውን ድርጅቶች ጭምር (ለምሳሌም ኢህአፓ፣ ኢዲዩ፣ …) ተዋግተው፤ ከዚህም አልፎ በህወሓትም ውስጥ የተለየ አስተሳሰብ ያራመዱ ወይንም ለሥልጣን ያሰጋሉ የተባሉትን እያሰቃዩና እየገደሉ በመሆኑ፤ መገዳደሉ በአንድ ሀገር ልጆች መካከል ከመሆን አልፎ በቤተሰብ መካከል ጭምር እንደነበር አሌ አይባልም። ለዚህ ደግሞ ሩቅ መሄድ ሳያስፈልግ በኢህአፓነቱ በወያኔ እንደተገደለ የሚነገረውን የአቶ በረከት ስምኦን ወንድም መጥቀስ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እንባዬን ጨርሼ፣ ደም እንደ እንባ አነባሁ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ሄኖክ የሺጥላ

ስደት

ወዳጄ እና ጓደኛዬ በቅርቡ በሱዳን አሳብሮ፣ በሊቢያ በረሃ አቋርጦ፣ በባህር አሳልጦ ጣሊያን፣ ከጣሊያን ደሞ ጀርመን እንደደረሰ አጫወተኝ። እርግጥ የተጓዘው መንገድ፣ ያየው መከራ፣ የቀመሰው ችግር እንዲህ በሁለት መስመር በሱዳን አድርጎ በሊቢያ አቋርጦ ጣሊያን ደረሰ ብሎ እንደማለት ቀላል አይደለም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግንቦት 20 እንዲህ መቀለጃ ሆና ትቅር?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ግንቦት 20 እንዲህ መቀለጃ ሆና ትቅር?ታዛቢ (ከአዲስ አበባ)

ሥራየ መምህርነት ነው። በአንድ የመንግሥት የ2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ውስጥ አስተምራለሁ። ሰሞኑን ታዲያ የግንቦት 20 የኢትዮጵያ የነፃነት ቀን እንደመሆኑ የበዓሉን መቃረብ አስታክኬ በየምገባባቸው በርካታ ክፍሎች ትምህርቱን ከመጀመሬ በፊት “እንኳን አደረሳችሁ” እላለሁ። ይሀንን የምለው ኢህአዲግ መራሹ ዴሞክራሲያዊው መንግሥታችን ጨቋኙን የደርግ መንግሥት ደምስሶ ህዝባዊ መሠረት የተላበሰና በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የቆመ የዴሞክራሲ ሥርዓት በመትከሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መቶ ሚሊዮን ህዝብ ያላት የሰው ድሃ ሀገር ኢትዮጵያ

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

Ethiopiaይገረም ዓለሙ

በ1982 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ወዴት እየሄደች እንደሆነ አይደለም የት ላይ እንዳለች አንኳን መናገር በማይቻልበት ወቅት፤ ከአንድ ባልንጀራየ ጋር እየሄድን፤ እኔ ከማላውቀው የእርሱ ጓደኛ ጋር መንገድ አገናኘን። እናም ሠላምታ ተለዋውጠው፤ ታዲያስ እንዴት ነህ፣ እንዴት ናችሁ ሲለው፤ ምን እባክህ ሰውም አለን ሰውም የለንም ሲል መለሰለት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦዴጎች ምን ነካቸው?

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ግርማ ካሳ

የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር (ኦዴግ). Oromo Democratic Front (ODF)

አንዳንድ በተለይም በውጭ ያሉ የኦሮሞ ብሔረተኞች፣ የአክራሪውን እና የብዙ ወገኖች ደም በእጁ ያለበትን የኦነግን ባንዲራ እያውለበለቡ፣ የጭቁን ኦሮሞ ወገኖቻችንን ተቃውሞ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም እና እንቅስቃሴውን ሃይጃክ በማድረግ፣ የኦሮሚያ ሪፑብሊክን ለመመስረት ያላቸውን ሕልም ለመተግበር ደፋ ቀና እያሉ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፍቅርና ክብር ለዚህ ነጻነትና ክብር ላበቁን ጀግኖች አርበኞቻችን!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

በፍቅር ለይኩን*

Ethiopian patriots. ጀግኖች አርበኞቻችን

"... When he saw a poster, Mussolini Invades Ethiopia, he was immediately seized by a violent emotion. At the moment, he writes, it was almost as if the whole of London had suddenly declared war on me personally. For the next few minutes I could do nothing but glare at each impassive faces, wondering if these people could realize that wickedness of colonialism, and praying that the day might come when I could play my part in bringing about the downfall of such a system. … I was ready to go through hell itself, if need be, in order to achieve my object."

ዕውቁ ፓን አፍሪካኒስትና የ"ጋና የነጻነት አባት" በሚል ቅጽል የሚጠራው ዶ/ር ክዋሜ ንኩርማ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ በሚያደርገው ጉዞው በለንደን ከተማ ባደረገው አጭር ጊዜ ቆይታ ያስተዋለው፣ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት ምልክት፣ የጥቁር ሕዝብ ታሪክ፣ ሥልጣኔ፣ ቅርስና ማንነት መገለጫ፣ የነጻነት የተስፋ ምድር- ከነዓን ተደርጋ የምትቆጠረው ኢትዮጵያ በፋሽስት ኢጣሊያ በግፍ የመወረር አስደንጋጭ ዜና፣ መርዶ በውስጡ ያሳደረበትን ስሜትና ቁጭት "ጋና" በሚል ርዕስ በጻፈው የሕይወት ታሪኩ መጽሐፍ ያሰፈረውን በጥቂቱ የቀነጨብኩት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ