እናት ኢትዮጵያ አደይ ኤርትራ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ከአንተነህ መርዕድ (ሚያዝያ 2007)
መሳይ መኮንንና ፋሲል የኔዓለም ወደ ኤርትራ ያደረጉት ጉዞ የብዙ ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም የኤርትራውያን ወንድምና እህቶች ቀልብ መሳቡ እሙን ነው። በተለይም የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ በብዙ መልኩ አስደምሞናል። እድላችን የተቆራኘነውና መነጋገሩና መብሰልሰሉ የሚገባ በመሆኑ ያለፍንበትን ሁሉ በትዝታ እንድፈትሽና አሁን የደረስንበትን እንዳይ ምክንያት ሆኖኛል። ነገሮችን ውስብስብና አጠቃላይ ከሆነ መልኩ ይልቅ ተጨባጭ ከሆኑ የግል ገጠመኞች ዙርያ ማውጋቱ የበለጠ ጉልህ ያደርገዋልና አንባቢዎቼም የራሳችሁ ገጠመኝ ዙርያ እየተሽከረከራችሁ የእኔን እንድትካፈሉ እጋብዛለሁ። በዚህ መልኩ ከምን ተነስተን የት እንዳለን ይታየናል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢህአዴግ ዕድሜ ስንት ነው?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዮሃንሰ ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

ወዲህ የሁለት ክርስቲያን ወዲህ ደግሞ የሁለት ወገን ደም እንዳይፈስ ቅዱሳን አባቶቻችን በፀሎትና በሽምግልና የተጉበት ጉዳይ ፍሬ አፍርቶ ከዛግዌ ሥርዎመንግሥት ወደ ሰለሞናዊ ሥርዎመንግሥት በሰላም ተሸጋገረች።ያለ ጠብታ ደም ይህ ከሆነ ስምንት መቶ ዓመታት ተቆጠረ። ከዚያ ወዲህ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ህዝብ እንደናፈቀው ገዥዎች እንደተሳለቁበት እነሆ ወያኔ ደራሲው አዘጋጁና ተዋናዩ የሆነበት "ምርጫ" ከፊታችን ቆሟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትግላችንን እንመርምር

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አንዱዓለም ተፈራ

ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ፤ “ትግላችን ወደፊት የሚሄደውና ለድል የሚበቃው፤ ሀገራዊ ራዕይ ይዘን፤ በአንድነት ስንሰለፍና ለአንድ ግብ ስንታገል ብቻ ነው!” በማለት አስፈላጊውን ውይይት ለማበረታታት ጽሑፎችን አቅርቤ ነበር። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ፤ አሁን ያለንበትን በመመርመር፤ ወደፊት ለመሄድ፤ አሁንም ወሳኝ የሆነው፤ በአንድነት መነሳታችን መሆኑን አሰምርበታለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የምንወድሽ ሀገራችን ደግመሽ አልቅሽ!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም:- ነጻነት ለሀገሬ)

የኢትዮጵያውያን/ት ህይወት ያሳስበናል!

እ.ኤ.አ. በ2005 ልክ የዛሬ 10 ዓመት በያዝነው ወር ገደማ አሁን በህይወት የሌለው እና እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ አድራጊ ፈጣሪ አምባገነን መሪ የነበረው መለስ ዜናዊ በዚያን ዓመት ተካሂዶ የነበረውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ተከትሎ ተከስቶ በነበረው ሁከት የደህንነት እና የጦር ኃይሉን በእራሱ ቁጥጥር ስር በማዋል በሰላማዊ እና ባልታጠቁ ንጹሀን ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እልቂት እና መከራን ያዘለ ዘመቻ አካሂዷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አደራጅተው ገደሉን፤ ተደራጅተን ብንገድልስ?

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

አብርሃም ዘታዬ
ፌዴራል ፖሊስ በሊቢያ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያኖች አስመልክቶ ለኀዘን የወጡትን ሲደበድብ

በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ ከደረሰብን ኀዘን ሳናገግም በሜዲትራንያን ባህር የሰጠሙ ወገኖቻችንን መርዶ ተረዳን። በአገር ቤት ከድሮም ጀምሮ በተናጥልም በጅምላም መጨፍጨፋችን አላቆመም። ባለቅኔው "ሞትና የላሊበላ ህንጻ ሁልጊዜ አዲስ ነው" ብሎ እንደተቀኘው ስለአዲሱ አሟሟታችን እንጉርጉሮ እናውጣለት ከተባለ በሰፈር ተደራጅተን እየሞትን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በመጨረሻም በግብጽ ነጻ ወጡ፣ እኛ ግን መንግሥት አለን እንዴ?

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ክንፉ አሰፋ
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ከሊብያ የተመለሱትን ኢትዮጵያውያኖች ሲቀበሉ

የፌስቡክ አርበኛው ቴድሮስ አድሃኖም ቦሌ ሄደው ከሊቢያ ነጻ የወጡ ዜጎችን ሲቀበሉ አየን። እፊታቸው ላይ የማፈር ሳይሆን የጀግንነት ስሜት ይነበባል። አቀባበላቸውም 90 ደቂቃ በኢንቴቤ የሚለውን ታሪክ ይመስላል። ኡጋንዳ ላይ የታገቱ ዜጎችዋን ለማስለቀቅ እስራኤል ያደረገችው ገድል። ቴድሮስ አድሃኖምም በኩራት እና በድል አድራጊነት ስሜት ነው ስደተኞቹን የተቀበሉት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ