የቀይ ባህሩዋን ፈርጥ-ጅዳን ያንቀጠቀጠው የዝናብና ጎርፍ (ክፍል 6)

ነቢዩ ሲራክ - ከሳውዲ ዐረቢያ

ክፍል አምስት መጣጥፌ የት ላይ እንደቆመ አሳምሬ አውቀዋለሁና ግራ አትጋቡ ... እውነት እላችኋለሁ ቀኑ ሲደርስ እቀጥለዋለሁ ... የዛሬው ከዚህ በፊት እንደማደርገው የኔው ሰበር ዜና መሆኑን አንድ ካላችሁ ወደ መረጃ ቅበላየ ላቅና ...

በመካከለኛው ምስራቅ በርሃ ተማክላ በምትገኘው ሳውዲ አረቢያ ጅዳና አካባቢዋ ክረምት የሚሉት ስሙ እንጅ ክረምቱ አይታዎቅም። በጅዳው ክረምት ቅዝቃዜው ከስንት አንድ ማታ ማታ በርታ ቢልም ዝናብ ግን ከአንድ ቀን ባለፈ ሲዘንብ አላስተዋልኩም። ይህ ከ15 አመት ባላነሰው የሳውዲ ቆይታየ የታዘብኩት ነው። በሃገሬ በኢትዮጵያ የሃምሌና ነሓሴ ዶፍ ዝናብ እኝኝ እያለ አላስገባ አላስወጣ ሲል ሲከርም እዚህ ሳውዲ የተገላቢጦች ሃሩሩ እያየለ የሙቀቱ መጠን እስከ 50 ዲግሪ ይደርሳል። ወርሃ ነሓሴ ሃገር ቤት ከርሞ የመጣ አንድ ወንድሜ በጠዋት የአዱ ገነት የሃምሌ ውርጭ አኮማትሮት ከሰአታት በረራ ረፋድ ላይ ጅዳ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሶ እንደወረደ ፊቱን የገረፈው የሙቀት ወላፈን ሲያስደምመው መክረሙ አይረሳኝም። ወንድሜ በሁኔታው ተገርሞና ተደንቆ ከሁለት ሰአት በረራ በኋላ ወላፈኑን ሞቃት የአየር ጸባይ ጅዳ ደረሰ። ሙቀት ሲያላጋው በሰአታት ልዩነት በሁለት ሀገራት መካከል ያየው የተፈጥሮ ጸጋ ልዩነት የገሃነምንና የገነትን ያህል ቢያከብደውም ወደ መጨረሻ በፈጣሪ ድንቅ ስራ ተስማምተን መለየታችን አይዘነጋኝም ። በሃገር ቤት "ብርዱ ምንቴስ ያስተቃቅፋል ..." በሚባልበት ወቅት በሳውዲ የሙቀቱ ወላፈን ፊትን እየገረፈ አቅልን እንደሚሰውር ማሳየት ከቻልኩ ወደ ሰሞነኛ ወጋወጌ ላቅና ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!