Mesfin Bezu of TG television* የምርጫው ትዝታዬ ... * የጅብ ችኩል ...

ነቢዩ ሲራክ

መቼም ይህ የአሜሪካ ምርጫ ከቅስቀሳው እስከ ትራንፕ ምርጫ ትዝታው ብዙ ነው። በመጨረሻው ቀንና በምርጫው ውጤት ቀን የሆንነው ግን በጣም ያጓጓና ልዩ ትዝታ ይዞ ያለፈ አጋጣሚ ነበር። ለብዙዎቻችን ... የማልረሳውን የእኔን ትዝታ ከትዝብት ጋር ላጋራችሁ ...

"እውነትን እንጂ ውሸትን አናስተናግድም!" የሚል መርኅን ይዘው ከሚንቀሳቀሱት የቲጂ ቲቪ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መስፍን በዙ "HILLARY WINS!" "ሂላሪ አሸነፈች!" የሚል አንድ አስገራሚ ሰበር መረጃ ከሌሊት 3:34 a.m. ተሰራጭቶ ደረሰኝ።

HILLARY WINS ከሚለው መረጃ ስር "ቲጂ ቴሌቭዥን ጠዋት ላይ የምርጫ ጣቢያዎቹን ጎብኝቶ ባገኘው መረጃ መሰረት ሂላሪ የአሜሪካ 45ኛ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል" በሚል የሚያትተው መረጃ አስገረሚ ነበር፤ መረጃው ለሂላሪ ደጋፊ ደስታ፣ ለትራምፕ ደጋፊ ኀዘንም ነበር ... መልዕክቱ እንደወረደ እንዲህ ነበር የሚለው፣

“TG Ethiopian Television did visit some polling stations this morning. Based on what the voters said, TG Ethiopian Television declares that Hillary Clinton will be the 45th President of the United States ...” ከጉጉቴ የተነሳ ደስታዬ ወሰን አጣና በሰፊው የመገናኛ ብዙኀን ማልጀ እስክሰማው የአቶ መስፍን መረጃ ነፍስ ዘርቶብኝ እረፍት ማድረጉን መረጥኩ።

እረፍት አይሉት እረፍት አድርጌ የእንጀራ ነገር ሆኖብኝ ወደ ሥራ ልሰማራ ረዥሙን መንገድ ስጀምር ግን "እውነትን እንጂ ውሸትን አናስተናግድም!" የሚል መርኅን ይዞ ከሚንቀሳቀሰው የቲጂ ቲቪ አዘጋጅ ጋዜጠኛ መስፍን በዙ "HILLARY WINS!"፣ “ሂላሪ አሸነፈች!” መረጃ “በሬ ወለደ” መሆኑን ተረዳሁ! አዘንኩ፤ ቢያንስ ጭብጥ ሳይያዝ ለምን መረጃ ይሰራጫል? ችኮላው ባላስፈለገ ብዬ ጋዜጠኛውን ሳማርራቸው፤ አጅሬ ጋዜጠኛ መስፍን በዙ ከወደ ምሽት ላይ ማስተባበያ አሰራጭተዋል፣ በተሰራጨው ማስተባበያም “የተሰራጨውን መረጃ እኔ በማላውቀው መንገድ፣ ከፍቃዴ ውጭ የተሰራጨ ነው!” ብለው ይቅርታ ጠይቀዋል ...

“It is true that when we talked to the voters in Virginia, most of them said that they voted for Hillary Clinton. Since we only talked to Virginia voters, please disregard the previous email. It was sent without my approval.”

Thank you

Mesfin Bezu

ያለጭብጥ መረጃ የጅብ ችኩል እየተኮነ “እውነትን እንጂ ውሸትን አናስተናግድም!” ቢሉት ፋይዳ የለውም! ከመረጃ ቅበላው እሽቅድድም፤ ለመረጃው ተዓማኒነት ቅድሚያ መስጠት እንደሚገባ የአቶ መስፍን በዙ ስህተት ካስተማረን መልካም ይመስለኛል!

ነቢዩ ሲራክ
ኅዳር 1 ቀን 2009 ዓ.ም.

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ